አሰብ ወደብ ላይ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የጦር ሰፈር ሊገነባ ነው።

በአቡዳቢ የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ መወያየታቸውን ተከትሎ በሀገራቱ ዙሪያ አዳዲስ ለውጦችን በማየት ላይ እንገኛለን።

ሁለቱ መሪዎች በተስማሙት መሰረት ኢትዮጵያ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ባድመን ጨምሮ አስራ ሰባት አወዛጋቢ የነበሩትን ወረዳዎች ለኤርትራ ለማስረከብ የተስማማች ሲሆን ኤርትራ በበኩሏ የአሰብ ወደብን ለኢትዮጵያ  በክፍያ እንድትጠቀምበት እንዲሁም የባህር ሀይል ጦር ሰፈር እንድትገነባበት ተስማምተዋል ፤ በስምምነቱ መሠረት ባህር ኃይሉ በአከባቢው በሚገኘው ኢምሬት የጦር ኃይል ቁጥጥር እንዲያደርግ ዋስትና ከኤርትራ አግኝቷል።

በቀጣይም የኤርትራ በጎ ፈቃደኝነት ከታከለበት በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በሌሎችጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል ። (ቆንጂት ስጦታው )