ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት ለሐሳቡ ጠንሳሽና የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ በዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስም እንድትሰየም ተጠየቀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት ሃሳብ ጠንሳሽ የነበሩትና የተረሱት የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ

በአርሲ ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም ነበር የተወለዱት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ከዚያም ከሼፊልድ ዩናይት በድጋሚ በፊዚክስ ሁለተኛ ዲግሪ ከከሎምቢያ ስቴት ዩንቨርሲቲ በአስትሮኖሚ/አስትሮፊዚክስ ደግሞ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ ወደሃገራቸው ተመልሰው ለ40 ዓመታት ያህል በመምህርነትና በተመራማሪነት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አገልግለዋል

ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በሃገራችን ታሪክ ብቸኛው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ የነበሩ ሰው ናቸው ። ከሶስት አመታት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ መስራች የነበሩም ሰው ናቸው።

በህዋው ሳይንስ ዘርፍ ለሃገራችን ቀዳሚ የነበሩት የኚህ ምሁር ባለቤት ዛሬ በታዲያስ አዲስ የራዲዮ ፕሮግራም ቀርበው ሲናገሩ እንደሰማናቸው,
ባለቤታቸው ሃገራችን በህዋው ሳይንስ ዘርፍ ተሳታፊ እንድትሆን ሳተላይት የማምጠቁን ሃሳብ ቀድመው ያስጀመሩና ለተግባራዊነቱ እስከእለተ ሞታቸው ይሰሩ የነበሩ ሰው ቢሆኑም አርብ እለት ትመጥቃለች ተብሎ ከሚታሰበው ሳተላይት ጋር ተያይዞ ስማቸው ሲነሳ አለመስማታቸው ቅሬታን እንደፈጠረባቸው ተናግረው አርብ እለት የምትመጥቀው ሳተላይት በባለቤታቸው ስም እንዲሰይምላቸው ጠይቀዋል ። 

በዚሁ ፕሮግራም ላይ ቀርባ ቅሬታዋን የገለፀችው የዶ/ር ለገሰ ወትሮ የ11 አመት ልጅም እንደተናገረችው ሃገራችን በህዋው ሳይንስ ቴክኖሎጂ የራሷ የሆነ ሳተላይት እንዲኖራት ሲደክሙ ዘመናቸውን ያሳለፉት የአባቷ ስም መረሳቱ እንዳስከፋት ገልፃ ዶክተር አብይ ቢቻል የሳተላይቷን ስም በአባቷ ስም እንዲሰየም እንዲያደርጉላት ይህ ባይሆን እንኳን ለፈር ቀዳጁ ተመራማሪ አባቷ በይፋ እውቅና እንዲሰጡላት ጠይቃለች።

እኛም የኋላው ከሌለ የፊቱ የለምና ታላቅ ህልም ይዘው ለሃገራቸው ሲሰሩ የነበሩትን እኚህ ሰው መርሳት አግባብ አይደለምና የሚገባቸውን ክሬዲት የኢትዮጵያ መንግስት ይሰጣቸው ዘንድ እንጠይቃለን። በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ያረፉት ዶ/ር ለገሰ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ ።