ምንም የተጀመረ የውህደት ንግግር የለም:: ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው – አቶ ናትናኤል ፈለቀ የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


– ብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ በጋራ ጥምር መንግስት ለመመስረት ቅድመ መግባባት ላይ ደረሱ

ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነውአቶ ናትናኤል ፈለቀ

በብልፅግናና በኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች መሃል የተደረሰው ሚስጥራዊ ንግግር ውህደት ሳይሆን ከምርጫው በኋላ አንዳቸው መንግስት መመስረት የሚያስችል መቀመጫ ባያገኙ በጋራ ጥምር መንግስት ለመመስረት ቅድመ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ነው።

የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ናትናኤል ፈለቀ ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው ሲል አስተባብለዋል። ኃላፊው እንደገለጹት ዘገባውን አስመልክተው ይመለከተዋል ላሉት ግለሰብ ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

መረጃውን ያደረሱን ምንጮች እንዳሉት ጠሚ አብይና ፕ/ር ብርሃኑ ይህን የተስማሙት የብልፅግና የፖለቲካ ፕሮግራም ከየትኞቹም ብሄር ተኮር ፓርቲዎች በተሻለ ከኢዜማ ፕሮግራም ጋር መቀራረብ ስለሚታይበት በመንግስት ምስረታ ሂደት ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮች አይኖሩም በሚል እሳቤ ነው።እነዚህ ሚስጥራዊ ውይይቶች መደረጋቸውን የሁለቱ ፓርቲዎች በርካታ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጭምር አያውቁም። ከ ምርጫ 97 በኋላ ቅንጀት አዲስ አበባን አለመረከቡ ስህተት እንደነበር ጠ/ሚ አብይ ለረጅም ጊዜ ፊት ለፊት ከሚቀርቡት ሰዎች ጋር ይሞግት እንደነበር አንድ ምንጭ  ነግረዋል። አሁንም ብልፅግናና ኢዜማ አዲስ አበባን ጠቅልለው ለማሸነፍ የምርጫ ግብግብ ውስጥ የሚገቡ ቢሆንም ጠ/ሚ አብይ ግን ኢዜማ በርካታ መቀመጫዎችን ቢያሸንፍም ስጋት ይሆናል ብሎ ስለማያስብ ስውር ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል። ምንጮች እንዳሉት ።

የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ናትናኤል ፈለቀ ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው ሲል አስተባብለዋል። ኃላፊው እንደገለጹት ዘገባውን አስመልክተው ይመለከተዋል ላሉት ግለሰብ ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በትዊተር ገፃቸውም ምንም የተጀመረ የውህደት ንግ ግር የለም የሀሰት ዜናውን ላሰራጨው ተቋም እርማት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል።እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ኃላፊነት የሚሰማቸው የመገናኛ ብዙኃን እንደሚፈልግ ፅኑ እምነታችን ነው።ሲሉ ጽፈዋል።