‹‹ውህደት በራሱ መፍትሔ አይደለም›› – ፕሮፌሰር መረራ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢህአዴግ ውህደት ስኬት የሚለካው በቀጣይ በሚሰራቸው ሥራዎች እንደሆነ ፖለቲከኞች ተናገሩ
(ኢ.ፕ.ድ)

Image may contain: 3 people, eyeglasses and closeup

አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ከአራቱ ግንባር ድርጅቶች ወደ ውህድነት በመምጣቱ ስኬታማ ከሆነ ለሌሎች ፓርቲ ዎችም አርዓያ እንደሚሆን የፓርቲ አመ ራሮችና ፖለቲከኞች ገለጹ። ስኬቱ የሚለካው ከውህደት በኋላ በሚያሳየው ለውጥ መሆኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪ ዎች፤ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ ችግሮችን በመቅረፍ መልካም አስተዳደር የሚያሰፍን ከሆነ ለሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችም አርዓያ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የመድረክ እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ዋናው ጉዳይ የፓርቲው መዋሃድ ሳይሆን የሚያመጣው ለውጥ ነው። ፓርቲው ለውጥ ካመጣ አርዓያ የማይሆንበት ምክንያት የለም። ካልተሳካለት ግን መጥፎ ምሳሌ ነው የሚሆነው። ‹‹ውህደት በራሱ መፍትሔ አይደለም›› የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ፤ ዋናው ጉዳይ የተዋሃደው ምን ለመሥራት ነው የሚለው እንደሆነ ተናግረዋል። ማንም ፓርቲ ቢሆን መጥፎ ፓርቲ መሆን አይፈልግም፤ ውጤታም ፓርቲ ለመሆን ግን ችሎታ ነው የሚወስነው።

ውህድ ፓርቲ መሆኑ በራሱ ህብረ ብሄራዊነትን ያመጣል ማለት እንደማያስችል የአፍሪካ ተሞክሮም እንደሌለ ይናገራሉ ፕሮፌሰር መረራ።

በንጉሳዊ ሥርዓቱም፣ በወታደራዊ የደርግ ሥርዓትም የነበረው ተሞክሮ አገሪቱን የጎዳ ነበር።

ለ27 ዓመታት የቆየው ኢህአዴግም የፌዴራሊዝም ሥርዓትን አሰፍናለሁ ብሎ አገሪቱን ሲያምስ የነበረ ነው። አዲሱ ውህድ ፓርቲ ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ፈተናዎች ማለፍ የሚችል ከሆነና ሀቀኛ የፌዴራሊዝም ሥርዓት የሚዘረጋ ከሆነ ነው መዋሃዱ ለውጥ አምጥቷል የሚባለው። ሀቀኛ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ካልዘረጋ ስሙን ስለቀየረ ብቻ ለውጥ ነው ማለት አይቻልም።

ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=23387