የምግብ መመረዝ አልተከሰተም – ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ

Image may contain: 6 people, people smiling, people standing and suit

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።ኢንጂነር ታከለ በስፍራው የተገኙት በትናንትናው እለት በተማሪዎች ላይ የማስመለስና የሳል ምልክት ታይቷል መባሉን ተከትሎ ነው።

በምልከታቸውም የሆስፒታል የምርመራ ውጤትን ጠቅሰው በተማሪዎች ላይ ከምግብ ጋር የተያያዘ ችግር አለመከሰቱን አስታውቀዋል።የምግብ መመረዝ አለመከሰቱን ያነሱት ከንቲባው በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የምገባ ፕሮግራም በተጠናከረና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።

አያይዘውም ፕሮግራሙ በሕግ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ሆኖ ይፀድቃል ማለታቸውን ከምክትል ከንቲባው የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ዛሬ ጠዋት በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ደረሰ የተባለውን ሁኔታ ተመልክቻለው።
ከምግብ ጋር የተያያዘ ችግር የለም። የሆስፒታል ምርመራ ውጤቱም የሚያሳየው እውነት የምግብ መመረዝ አይደለም።
ለማንኛውም የምገባ ፕሮግራም በተጠናከረና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይቀጥላል:: በሕግ ደረጃም በከተማችን ምክር ቤት አዋጅ ሆኖ ይፀድቃል። ተማሪዎች እና ቤተሰቦች፤ ከተማ አስተዳደራችን የትምህርትን ሥራ አንዱ እና ቁልፍ የልማት ሥራችን እንደሆነ እንደገና እርግጠኛ ሆኜ አረጋግጥላችኋለሁ።

Source – Takele Uma Banti

Image may contain: 5 people, people smiling, people standing