በአርባምንጭ የመከላከያ ሰራዊት ያሰረውን አክቲቪስት ሊፈታው እና በከተማዋ ወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ወከባ እና ሕገወጥነት ሊያቆም ይገባል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአርባምንጭ የመከላከያ ሰራዊት ያሰረውን አክቲቪስት ሊፈታው እና በከተማዋ ወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ወከባ እና ሕገወጥነት ሊያቆም ይገባል። ፍትህ ለዳዊት ዋሲሁን !!!

ዳዊት ዋሲሁን ካሳ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥይት ስለተመታ ወጣት በገፁ ላይ አስፍሯል ይህን በፃፈ ማግስት ከጥዋቱ 4:00 አካባቢ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታስሯል። የዳዊትን መታሰር ስዩም ተሾመ በሰማ ሰዓት ወደዞን አስተዳደሪ አቶ ብራሃኑ ዘውዴ ጋ በመደወል የተፈጠረው ነገር ጠየኩት ማታ ከፃፈው ፁሁፍ ጋር በተያያዘ እንደያዙት እና ለፃፈው ፁፈም ይቅርታ ጠይቆ ፁፉንም አስተካክሎ ተግባብተው እንደተለቀቀ ተነገረኝ።

ዳዊት የፃፈውን ፁሁፈ እውነታ ለማጣራት በጥይት ተመታ ወደተባለው ወጣት አርባምንጭ ሆስፒታል አመራው በጥይት የተመታውም ወጣት ዳዊት የፃፈውን ፁሁፍ እውነት እንደሆነ አረጋገጠልኝ ወጣቱን በጥይት የመቱት የከተማ ፖሊስ ወይንም ልዩ ሀይል ሳይሆን የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደሆኑ ነገረኝ የራጅ ውጤቱም በጥይት ስለመመታቱ ያረጋግጣል ይህንን መረጃ ሁሉ በቪዲኦ ቀረፅኩት ለማስረጃነት ይሆን ዘንድ ከታች አስቀምጨዋለው።

በተጨማሪ በዳዊት ገፅ ላይ የሰፈረው የማስተካከያ ፁፍ በዳዊት እንዳልተፃፈ እንዲሁም ስልኩን ወስደውበት የFB password አስገድደው በመውስድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደፃፉት ለማወቅ ችያለዉ። ታድያ ለምን የመከላከያ ሰራዊት ዳዊትን ሊያስር ቻለ እንደ እኔ እይታ ከሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዳዊትን ሊያስር የቻለው በሰራዊቱ አባላት የተፈጠረውን ስህተት ለመሸፈን እና እራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን ነው።

ዳዊት እስካሁን ታስሮ ነው ያለው ከቤተሰቡ ወጪ ማንም እንዳያገኘው ተከልክሏል ምግብም በሰአቱ እያደኘ አይደለም። ከታሰረ 24 ሰዓት ያለፈው ሲሆን እስካሁን ፈርድ ቤት አልቀረበም ወደ ጣብያም አልተወሰደም ህግ አስከባሪ ህግ እየጣሰ ነው። በአጠቃላይ የአካባቢውን ሰላም ለማወክ በህግ አካላት እሚደረጉ ፀባጫሪ ድርጊቶች ባስቸኳይ ይቁም !!!

ፍትህ ለዳዊት ዋሲሁን !!! #MinilikSalsawi