እጅ እና እግር የሌለው አካል ጉዳተኛ ራስ ዳሽን ተራራን ወጣ

እጅ እና እግር የሌለው እንግሊዛዊ አካል ጉዳተኛ ራስ ዳሽን ተራራን ወጣ

EBC : ሙሉ በሙሉ እጅ እና እግር የሌለው እንግሊዛዊው አሌክስ ሌዊስ የተባለው የአካል ጉዳተኛ በኢትዮጵያ ትልቁን የራስ ዳሽን ተራራ መውጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአፍሪካ ከሚገኙት ታላላቅ ተራሮች አንዱ የሆነውን የራስ ዳሽን ተራራን በልዩ ሁኔታ በተሠራች የአካል ጉዳት ተሽከርካሪ በመታገዝ፣ በደረቱ እየተሳበ እና በገመድ በመታገዝም ጭምር እስከጫፍ ድረስ መውጣቱ ታውቋል።

ይኸው እንግሊዛዊ ከስድስት ዓመታት በፊት ባጋጠመው ለሕይወት አስጊ የሆነ ሕመም የተነሣ ሁለት እጆቹንና ሁለት እግሮቹን ከማጣቱ በተጨማሪ ፊቱ ላይም ጉዳት አጋጥሞታል።

አካል ጉዳተኛው ተራራ ወጪ አሌክስ ይህንን ለማድረግ የተነሣሣው ሳም የተባለው የስምንት ዓመት ወንድ ልጁ ማድረግ የሚፈልገውን ነገር ለማድረግ የትኛውንም ዓይነት የአካል ጉዳት እንደማያግደው ለማሳየት ያደረገው መሆኑን ገልጿል።

Image may contain: 2 people, outdoor

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US