በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ መከሰቱ ታወቀ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ ተከሰተ

(ኤፍ ቢ ሲ) በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ መከሰቱን የቃፍታ ሁመራ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
እሳቱ ትናንት ማምሻውን የተነሳ ሲሆን እስካሁን በ1 ሺህ 500 ሄክታር የፓርኩ ክፍል ላይ ጉዳት ማድረሱን የፓርኩ ፅህፈት ቤት ገልጿል።

Image may contain: one or more people, people standing, sky, outdoor and natureእሳቱ በህገ ወጦች ምክንያት የተከሰተ ሊሆን እንደሚችልም የፓርኩ ፅህፈት ቤት ተወካይ አቶ ሃብቶም ሃጎስ ተናግረዋል።

የእሳት አደጋው በፓርኩ በወራውራ፣ ጠበቆ፣ ኮርቸሊት እና ሰሊንጎቦ ቀጠናዎች መከሰቱንም ነው የተናገሩት።

እሳቱ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ በጥበቃ ሰራተኞች ለመቆጣጠር መሞከሩን ጠቅሰው፥ የአካባቢውን ነዋሪዎች በማስተባበር ለመቆጣጠር መታቀዱንም ገልጸዋል።

የሚመለከታቸው አካላትም በፓርኩ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ መረባረብ እንደሚኖርባቸው ጠቁመው፥ እሳቱን ለማጥፋት ለሚደረገው ርብርብም በስፍራው ያሉ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ከኤርትራው ብሔራዊ የዝሆኖች ጥበቃ ስፍራ የሚዋሰን ሲሆን፥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዘጠኝ የዝሆን መገኛዎች ውስጥ አንዱ ነው።

Image may contain: fire, outdoor and nature