3 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አለመምጣታቸው ተገለጸ!

በትምህርት ዘመኑ 3 ሚሊየን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አለመምጣታቸው ተገለጸ!

በትምህርት ገበታ ላይ እንዲውሉ በእቅድ ከተያዘው 28 ሚሊየን ተማሪዎች ውስጥ 3 ሚሊየን ያክሉ ወደ ትምህርት ገበታ አለመምጣታቸው ተገለጸ። የትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው እለት ባቀረበው 1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸሙ የዝግጅት ምዕራፉን እና የተማሪዎችን ምዝገባ የተመለከቱ ሪፖርቶችን አቅርቧል።

በሪፖርቱም በዚህ አመት በትምህርት ገበታ ላይ እንዲውሉ በእቅድ ከተያዘው 28 ሚሊየን ተማሪዎች ውስጥ እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ 6 ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዳልመጡ ተገልጿል። በተሰሩ ስራዎች 3 ሚሊየኑን ወደ ትምህርት ቤት ማምጣት መቻሉን ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላየ ጌቴ ተናግረዋል። በቀጣይ ከትምህርት ገበታቸው የቀሩ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለማምጣት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

Via FBC


► መረጃ ፎረም - JOIN US