ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከግጭት አውድ በመቆጠብ ፍሬያማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስምሪት ላይ ሊያተኩር ይገባል – ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከግጭት አውድ በመቆጠብ ፍሬያማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስምሪት ላይ ሊያተኩር ይገባል – ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከግጭት አውድ በመቆጠብ ፍሬያማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስምሪት ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

ሀገር አቀፍ የስራ ዕድል ከፍተኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ላይ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የልማት አጋሮች፣ የግል ዘርፍ ተዋናዮች፣ የወጣትና ሴት ማህበራት ተወካይ የሆኑ ከ450 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ጉባኤው “አመርቂና ዘላቂ የስራ እድል ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ጉባኤውን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፥ ወጣቱ ትውልድ ከግጭት አውድ ራሱን በመቆጠብ ፍሬያማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስምሪት ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ንብረት እየወደመ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ደመቀ፥ይህም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዳከም ባለፈ በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው መሆኑን አብራርተዋል።

መንግሥትም ለሁሉም ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር አስቻኳይ ሁኔታዎችን ደረጃ በደረጃ እንደሚያመቻች ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በቀጣይ ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ውጤታማ ለማድረግም የሀገርን ሰላም ማስጠበቅ ቅድሚያ ተሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ በግሉ ዘርፍ የተመራ፣ በዕውቀት የሚመራ ስራ በመፍጠር ሁሉም እጆች የሚሳተፉበትና የሚጠቀሙበት ኢኮኖሚ መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል።

የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ኤፍሬም በበኩላቸው ፥በቀጣይ 10 እና 20 ዓመታት ሊተገበር የሚችል የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።

በዕቅዱ መሰረትም ወደ 20 ሚሊየን የሚጠጉ ወጣቶች በአዲሱ የስራ ዕቅድ ፈጠራ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።