የእምቦጭ አረም ለማጥፋት ሚሊዮን ብሮች ወጥቶባቸው የተገዙ ማሽኖችም ያለ ሥራ ቆመዋል ተባለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


VOA : በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ይዘው የቀረቡ ምሁራንና ግለሰቦች የሚያሰራቸው አካል እንዳላገኙ ተናገሩ።

በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት ሚሊዮን ብሮች ወጥቶባቸው የተገዙ ማሽኖችም ያለ ሥራ እንደቆሙ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ቅሬታ የቀረበበት የክልሉ የአካባቢ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

በቅርቡ የጣናን ጉዳይ እንዲከታተል የተቋቋመው የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በበኩሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተቀናጀና ቅደም ተከተላዊ በሆነ መንገድ የእንቦጭ አረምን ከጣና ሀይቅ ላይ አስወግዳለሁ እያለ ነው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።