ኢህአዴግ እራሱን አጥፍቶ እንዳያጠፋ እሰጋለሁ – ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ እራሱን እንዳያጠፋ እሰጋለሁ አሉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ግንባር ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ በሚል ሊዋሃድ እንደሆነ በመገለጽ ላይ ይገኛል።

ግንባሩ ወደ ፓርቲነት እቀየራለሁ ማለቱን ተከትሎ የተለያዩ ሃሳቦች ከምሁራንና ፖለቲከኞች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንፈረንስ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንዳሉት የኢህአዴግን አንድነት እኛ እንፈልገዋልን ፣ ኢህአዴግ እራሱን አጥፍቶ እንዳያጠፋ እሰጋለሁ ብለዋል፡፡

ኢህአዴግ አሁን ያለበትን ችግር ካልፈታ ወደ ከፋ ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ ፣መከፍፈል አደጋ ሊገባ ይችላል ይህ ደግሞ እኛንም ወደ አደጋ ይዞን ይገባል ፣ ሽግግሩ ወደ ሌላ ቀውስ እንዳያማራ ኢህአዴጎች ደጋግመው የቤት ስራቸውን መስራት አለባቸው ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ።

የኢህአዴግ አንድነት ከ ኢህአዴግ በላይ እኛ እንፈልገዋልን ፣ ኢህአዴግ እራሱን አጥፍቶ እንዳያጠፍ እሰጋለሁ ብለዋል፡፡

በሀገራችን ያሉትን ዋና ዋና ችግሮች መፍታት ያልቻልነው የሁላችንም አይን ስልጣን ላይ ብቻ ስለሆነ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መረራ የኢህአዴግ ውህደት አገሪቱ ከገባችበት ወጥረት በሚያወጣ መንገድ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢህአዴግ ውህደት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ አይደለም ፣ በተገቢው መንገድ መታየት አለበት መንግስቱ ሐይለማሪያምም ከ5 ፓርቲዎች ጋር ውህደት ፈፅመው ነበር ሀገሪቱን ከቀውስ አልታደጋትም እንጂ ብለዋል፡፡

ኢህአዴግ አንድም ሆነ አስር እኛ ከ50 አመት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተርምስ እንዲፈታ እንፈልጋለን ፣ ይህን ከአደረጉ እንደግፍቸዋለን ካልሆነ ግን ትግሉን ከመቀጠል ውጪ አማራጭ የለንም ብለዋል ፕሮፌሰሩ፡፡

ፕሮፌሰር መረራ “ኢትዮጵያ ወደ ብሔራዊ መግባባት እንድታመራ ሁሉም የቤት ስራውን መስራት አለበት፣ መደማመጥ ፣ መቻቻል ፣ መወያየት እና መደራደር አለብን” ሲሉም የሀገር ጉዳይ ያገባናል ለሚሉ የፖለቲካ ሐይሎች እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ETHIO FM 107.8