የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ዝግጅት

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

የሲዳማ ብሔር የህዝበ ውሳኔ ማስፈጸሚያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በመጪው የኅዳር ወር መግቢያ ለሚያካሂደው ህዝበ ውሳኔ የዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ አንደሚገኝ አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አዳነ ገበየሁ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ጽሕፈት ቤቱ የክልሉ መንግሥትና የሲዳማ ዞን መስተዳድር በሕዝበ ውሳኔው የሁሉንም አካላት ጥቅምና ፍላጎት ለማጣጣም የሚያስችሉ አስተዳደራዊና የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ» ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ የዝግጅት ሂደቱ በደቡብ ክልል መንግሥትና በሲዳማ ዞን መስተዳድር በኩል መጓተቶች እንዳጋጠሙት እየገለጸ ይገኛል። ሸዋንግዛው ወጋየሁ ከሀዋሳ ዝርዝሩን ልኮልናል።