" /> የጥቅምት 2 ሰልፍ አዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን ቀልብ ስቧል። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የጥቅምት 2 ሰልፍ አዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን ቀልብ ስቧል።

የጥቅምት 2 ሰልፍ አስመልክቶ የውጭ አገር አምባሳደሮች ከጋዜጠኛ እና የባልደራሱ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ ማብራሪያ ጠየቁ -ባልደራሱ ምላሽ እየሰጠ ነው

Image may contain: 2 people, crowd and outdoor

የጥቅምት 2/2012 የአዲስ አበባውን በባልደራሱ ሕዝባዊ የተጠራ ሕዝባዊ ሰልፍ አስመልክቶ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች በአካል እና በስልክ ከሊቀመንበሩ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ማብራሪያ ጠይቀው ምላሽ እያገኙ መሆኑን ለማወቅ ተችሉዋል።
ይድነቃቸው ከበደን ጉዳዩን አስመልክቶ የጻፈውን ያንብቡ ሼር ያድርጉት

አዲስ አባባ

ሰልፉ የአምባሳደሮች እና የአታሺዎችን ቀልብ ስቧል !

የጥቅምት 2 ሕዝባዊ ሰለማዊ ትዕይንት አስመልክቶ በአዲስ መቀመጫቸውን ያደረጉ የውጪ አገራት አምባሳደሮች እና አታሺዎች ፤ ህዝባዊ ሰልፉን አስመልክቶ
እነሱ በጠየቁት መሰረት ፤ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ጋር፤ በስልክ እና በአካል ገለፃና ውይይት መደረጉ መረጃዎች እያመላኩት ነው።

ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ !!!
ይድነቃቸው ከበደ


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV