በአጣዬው ግጭት የሰሜን ሸዋ ዞንና የኦሮሞ ብሔር አስተዳደር እየተወዛገቡ ነው

DW : ሰሞኑን በአማራ ክልል አጣዬ አካባቢ የተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት፣« የአማራ ክልል በተለይም የሰሜን ሸዋ ዞን እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ኃይሎች ናቸው» ሲል የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታ መምሪያ አስታውቋል።የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር፣« አጣየን ለማጥቃት የተዘጋጀ እና የተደራጀ ኃይል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ አለ»ይላል።በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ በዞኑ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል ፈፅሞ የለም ባይ ነው።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውና 13 መቁሰላቸውን አመራሮቹ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE