ሕፃናትን የመመገቡ ሂደት መልካምነት የተፈናቀሉትንና የጎዳና ልጆችን የማያካትት ከሆነ ጎዶሎ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ለተራቡና ለታረዙ የጎዳና ልጆችና ለተፈናቀሉ ተማሪዎችስ ???

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

ሕፃናትን የመመገቡ ሂደት መልካምነት እንደተጠበቀ ሆኖ የተፈናቀሉትንና የጎዳና ልጆችን የማያካትት ከሆነ ጎዶሎ ነው። ካሁን ቀደም ጎዳና ተዳዳሪዎችን ለማቋቋም በሚል የተሰሩ ስራዎች ተድበስብሰው በየጎዳናው አሁንም ሕፃናት ፈሰው ይገኛሉ።

የሰብዓዊነት ፖለቲካ የተፈናቀሉትንና ጎዳና ተዳዳሪዎችን ሊያካትት ይገባል።ሕፃናትን የመመገቡ መርሐ ግብር መልካምነት ከቤታቸውና በትምሕርታቸው የተፈናቀሉትን ቢያካትት ሙሉ ይሆናል። በርካቶች ከአዲስ አበባ በሕገወጥነት ሰበብና በስርዓት አልበኛ ወጣቶች መፈናቀላቸው የአደባባይ ሐቅ ነው።

ከተለያዩ የመዲናዋ አከባቢዎች ከቤታቸውና በትምህርታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ለቅሷቸው ሊሰማ ይገባል። በትምሕርታቸው ላይ ያሉትን ሕፃናት እስከተረዱ ድረስ ሌሎችም ሊረዱ ይገባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰብዓዊነት የፖለቲካ ንግድ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ ይሆናል።

ሰብዓዊነት ከተባለ ሁሉንም ሊያካትት ይገባል ስንል ለመልካምነት ምስጋና እንዳለው ሁሉ ለሰሞነኛ የፖለቲካ ፍጆታ የሚደረጉ ፕሮፓጋንዳዎችንም ለመተቸት እንገደዳለን።ሰብዓዊነት በግልና በቡድን የፖለቲካ ትርፍ ላይ ከተመሰረተ አደጋው የከፋ ነው። #MinilikSalsawi