" /> የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ የእርቅ ሳምንት አወጀ። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ የእርቅ ሳምንት አወጀ።

የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ሀብረት የእርቅ ሳምንት አወጀ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት የ2012 የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ የእርቅ ሳምንት አወጀ።

የእርቅ ሳምንቱ ከመስከረም 9 እስከ መስከረም 22 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

Image may contain: 7 people

የእርቅ ሳምንቱ የታወጀው በ2012 ዓ.ም መስከረም 24 እና 25 በተከታታይ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ የሚከበሩ የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተገልጿል።

አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንዳስታወቁት፥ የእርቅ ሳምንቱ የታወጀው ሰማይና ምድሩን በማስታረቅ በሰላምና በፍቅር የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ነው።

የ2012 አዲስ ዓመትም የሰላምና አደስታ እንዲሆንም የኦሮሞ አባ ገዳዎች ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና ቀን የሆነው ኢሬቻ በዓል በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።

የመጀመሪያው የክረምት መውጣትን ተከትሎ በውሃማ አካባቢዎች የሚከበር ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ በበልግ ወቅት በተራራማ አካባቢዎች ይከበራል።

ተቋርጦ የነበረውን “የሆራ ፊንፊኔ” ኢሬቻ በዓልንም በአዲስ አበባ ለማክበር አስፈላጊው ቅደመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረትና የኦሮሚያ ቱሪዝም ቢሮ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV