አንዱ ብሄር ለሌላው ብሄር ኩራትና ክብሩ ነው – አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

አንዱ ብሄር ለሌላው ብሄር ኩራትና ክብሩ ነው- የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም

(ኤፍ.ቢ.ሲ) አንዱ ብሄር ለሌላው ብሄር ኩራት እና ክብሩ ነው አሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም።

የብሄራዊ የኪራት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ “አዲስ አበባ ቤቴ ኢትዮጵያዊነት ኩራቴ” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የአዲስ አበበ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች እና እንግዶች ተገኝተዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግርም፥ ለመላው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚከበረው ብሄራዊ የኩራት ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም አክለውም፥ ኢትዮጵያውያን የገናና ታሪክ ባለቤት፣ የስልጣኔ መሰረትና ተምሳሌት የሆነች የሀገር ያለችን ኩሩ ህዝብ ነን ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ለማንነታችን እና ለሀገር ሉአላዊነት የማንደራደር ብዙ ሆነን አንድ የሆንን ታላቅ ህዝብ ነን፤ ኢትዮጵያውያን ለአፋኝ እና ጨቋኝ አምባገነናዊ ስርዓት የማንበረከክ በእኩልነትና በመቻቻል የምንተማመንና በተግባር የምናረጋገጥ ጨዋ ህዝብ ነን ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያውያን ተከባበረን እና ተደጋግፈን ማደግ እንደምንችል በተግባር ለዓለም ህዝብ ያሳየን ታላቅና ጨዋ ህዝቦች ነን ብለዋል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ።

ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ ታሪኮች ፣ አመለካከቶች፣ ፍላጎቶችን ያየዘች ፀጋችነችም ብለዋል።

አንዱ ብሄር ለሌላው ብሄር ኩራት እና ክብሩ ነው ያሉት አፈጉባዔዋ፥ አንድ ሀይማኖት ለሌላው ሀይማኖት ኩራትና ክብሩ ነው፤ ስጋት የሚሆንብን ማንነት ወይም ብሄር ከቶ የለንም ሲሉም ተናግረዋል።

ብሄራዊ የኩራት ቀን ሁሌም እንደኮራን እንደተከባበርን ከፍታውን ያለምንም ችግርና ስጋት እየተሸጋገርን እነድንቀጥል ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኩራታችን ምንጭ የሆነውን ህብረ ብሄራዊ አንድነት ይበልጥ የማጠናከር ግዴታ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።

አንዱ ብሄር አለንዱ ኩራትና ጌጥ ነው፤ ኢትዮጵያውያን አንዳችን ያለአንዳችን መኖር የማንችል ልዩ ፀጋ ያለን ኩሩ ዝህብ ነን ሲሉም ተናግረዋል።

በቀጣዩ የ2012 አዲስ ዓመትም የሁሉም የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሰላምና ደህንነት ተጠብቆ ዓመቱ ሙሉ የደስታና የኩራት ጊዜ እንዲሆን ተመኝተዋል።