በበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image may contain: 1 person, beardበበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አርቲስት ተዘራ ለማ ትናንት ምሽት ቤቱ ውስጥ እያለ በድንገት ህመም ካጋጠመው በኋላ በአካባቢው ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል ቢወሰድም ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

“ውሳኔ ፊልም” ላይ መጀመሪያ የትወና ስራውን የሰራው አርቲስት ተዘራ ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ተጫውቷል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ፥ ፍቅር ባጋጣሚ ፣ ታስጨርሽኛለሽ፣ ፍቅር በይሉኝታ፣ አልወድሽም፣ ወንድሜ ያቆብ፣ ኢንጂነሩ እና ጥቁር እና ነጭ ተጠቃሽ ናቸው።

አርቲስት ተዘራ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

ነብስ ይማር!