አዲስ አበባ ላይ መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች አማረሩ።

DW : የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች አዲስ አበባ ላይ እንደወትሮው መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን አማረሩ። እነዚህ ወገኖች የአዲስ አበባ አስተዳደር የመንገድ ትራፊክ አስተዳደር ኤጀንሲ ከባድ መኪናዎች ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት በመዲናዋ እንዳይንቀሳቀሱ ማገዱ ለችግር ተዳርገናል ይላሉ።የከባድ መኪና አሽከርካሪዎቹም ሆኑ ባለንብረቶቹ በተጠቀሰው ደንብ ምክንያት እንደከዚህ በፊቱ በቀን ተንቀሳቅሰው ቤተሰቦቻቸውን መመገብም ሆነ የባንክ ዕዳቸውን መክፈል እንዳልቻሉ ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE