የመምሕራን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው። …… ሊባረር የታቀደለት የመንግስት ሰራተኛውም !

የመምሕራን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው። …… ሊባረር የታቀደለት የመንግስት ሰራተኛውም ! …. የስራ ማቆም አድማ ማንን ገደለ ? ….. ደሞዛቸውን ማጣታቸው ብቻ ሳይሆን ለእስር መዳረጋቸውም በእውቀት አባቶች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ በግልጽ ያሳያል። ይህን ግፍ የሚቃወም ወይንም የሚያስቆም የመምህራን ማሕበር አለመኖሩም ያስቆጫል።

………… አለ የሚባለው መምሕራን ማሕበርም የመንግስት አፋሽ አጎንባሽ ሆኖ ዝምታን መርጧል። ……….. ሌላው ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች የሕልውና ጉዳይ ነው። ደምወዝ ለመንግስት ሰራተኞች መክፈል ያቃተው የሙስናው ኢምፓየር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞችን በአዋጅ ለማባረር እያሟሟቀ ይገኛል። ለሰራተኛው የሚታገል የሰራተኛ ማሕበር አለመኖሩ ያማል።

……. በዚህ ኑሮ ውድነት ጣራ በነካበት አስቸጋሪ ጊዜ ላይ በመምሕራን እና በመንግስት ሰራተኞች ላይ የሚፈፀመው ግፍ እጅግ ዘግናኝ ነው። እንዲህ አይነት በግልፅ የሚታዩ በደሎች፣ግፎች እና ጫናዎች ሲልም የደምወዝ ዘረፋ ሲፈፀም መንግስት እምቢተኛ ሲሆን እና መፍትሄ ሲጠፋ ማሕበራት ወይንም የተደራጁ ሃይሎች የስራ ማቆም አድማ ይጠራሉ፤ በተለይ የመንግስት ሰራተኛው …… !!

ከመኖሪያው ብቻ ሳይሆን ከስራውም የሚፈናቀለው ዜጋ ለመብቱ መታገል ይገባዋል። …….. ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ! የምንለው ወደን አይደለም። #MinilikSalsawi