የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ እስካሁን አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸውን መግለጡን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ትምህርት ቢሮው ዘንድሮ ከቅድመ አንደኛ እስከ ኹለተኛ ደረጃ ድረስ 7 ሚሊዮን 71 ሺሕ 933 ተማሪዎች ለመመዝገብ አቅዶ፣ እስካሁን የመዘገበው 2 ሚሊዮን 543 ሺሕ 128 ተማሪዎችን ብቻ እንደኾነና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች አኹንም ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑ ገልጧል ተብሏል።ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ትምሕርት ቤቶችን በድሮን የሚያወድመው እንዲሁም በእሳት የሚያቃጥለው የአብይ ሰራዊት ነው።
የብርሃኑ ጁላን ጦር ሰላማዊ አድርጎ ያቀረበው ቢሮው ትምህርት ቤቶች በታጠቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና የመምህራን ግድያ መኖሩም በትምህርት ላይ ጫና እንዳሳደረ ቢሮው መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። በርካታ ትምሕርት ቤቶች በአብይ አሕመድ በድሮን እና ብጦር አይሮፕላኖች ተደብድበው መውደማቸው ይታወቃል ።