ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስን አገዱ

የሠራተኛ ቅጥር እንዳይፈጽሙ እና ከፍተኛ ወጪዎችን እንዳያንቀሳቅሱ አገዱ፤ የመሪ ዕቅድ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ለጽ/ቤቱ የ5 ከፍተኛ ባለሞያዎችን ቅጥር በውድድር ለመፈጸም እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት የተላለፈ እግድ ነው፤ ከፍተኛ ወጪዎቹ፡- በጀታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ፣ የ2 ሕንፃዎችንና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ አዳራሽ ዲዛይን፣ ግንባታና ቁጥጥር ሥራን እንዲሁም የአህጉረ ስብከት ተሽከርካሪዎች ግዥ አፈጻጸምን ይመለከታሉ፤ በነውጠኞች ጥፋት ለተጎዱት የሶማሌ አብያተ ክርስቲያን እድሳት …