ኦዴፓን ከሞት ያነሳሁት እና ስሙን ያደስኩለት እኔ ነኝ። ከእኔ ጋር (ኦዴፓ) እንዲህ ዓይነት ሳፋጣ ቢያቆሙ ይሻላቸዋል። – ጃዋር መሃመድ

ከደረጀ ሃብተወልድ

ለምን እውነቱን አወጣብኝ ብሎ ኢሳትን የከሠሰው ኦዴፓ እንደሚከተለው በOMN ኃላፊ በተራው ተከሷል፣ ማስጠንቀቂያም ተሰጥቶታል:-

“ትናንት ምሽት የጃዋርን OMN ቲቪ ስመለከት አቶ ጃዋር ቃለ ምልልስ እየሰጠ ነበር:: ውይይቱ የተካሄደው በኦሮምኛ ቋንቋ ሲሆን ዋንኛው ማጠንጠኛው “ኦዴፓ” እና ወቅታዊ “መግለጫው” ነበር::

ቃለመጠይቅ አቅራቢው አቶ ተስፋዬ:- “ኦዴፓ በፓርቲዬ እና ኦሮሞ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብናል” ያለው አንተን አፍህን ለማዘጋት ነው እያሉ ነው:: አንተ ምን ትላለህ?” ሲል ጃዋርን ጠይቆታል:: ጃዋር እንዲህ ሲል መልሷል:-

– ኦዴፓን ከሞት ያነሳሁት እና ስሙን ያደስኩለት እኔ ነኝ:: ከእኔ ጋር (ኦዴፓ) እንዲህ ዓይነት ሳፋጣ ቢያቆሙ ይሻላቸዋል::
– ኦዴፓን እያዳከሙ ያሉት በውስጡ የተሰገሰጉ የድሮው ኦህዴድ ሌቦች ናቸው!!
– ገላን ላይ 500 ሄክታር መሬት የሸጡ ሌቦች እሁንም ኦዴፓ ውስጥ በሥልጣን ላይ አሉ::
– ሰበታ ላይ በሌለ ድርጅት ስም 40 ሄክታር መሬት የሸጡ ሌቦች አሁንም በኦዴፓ ሥልጣን ላይ ናቸው::
– ወለጋ ላይ ኦነግ ባንኮችን ሲዘርፍ አብረው ያዘረፉ እና የተካፈሉ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት አሉ::
– ወለጋ ላይ የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ካምፕ እንዳይገቡ የሚያደርጉት የኦዴፓ ሰዎች ናቸው:: ምክንያቱም ባንክ ዘርፈው መካፈላቸውን ምስጢር እንዳያወጡባቸው ነው::
– ታከለ ላይ የሚነዛው ጥላቻ ምንጩ ከኦዴፓ ከእራሱ ውስጥ ካሉ ሌቦች ነው::
– የለማ እና የዐብይ ሥርዓት እየፈራረሰ ነው::
– የኦሮሚያ መንግሥት በሙሰኞች እና በሌቦች ሽባ (paralyzed) ሆኗል::

ይህን ያለው የኢሳት ዳይሬክተር ቢኾን ኖሮ …. ብላችሁ አስቡት።

ለትርጉሙ ዮሐንስ መኮነንን እናመሰግናለን።