«በምዕራብ ጎንደር ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ጦርነት ይካሄዳል» ነዋሪዎች

አንድ የመተማ ዮሐንስ ነዋሪ«ዛሬ በከተማዋ የተኩስ ድምፅ ባይሰማም፣ በትናንትናው የተኩስ ልውውጥ የ2 ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል»ብለዋል፡፡በከተማዋ ከሰኞ ጀምሮ እንቅስቃሴዎች እንደሌሉም ተናግረዋል። ሌላ አስተያየት ሰጭ የፋኖ ታጣቂዎች በመተማ ወረዳ የሺንፋ ከተማን ያለምንም ተኩስ ትናንት ማምሻውን እንደተቆጣጠሯትም አስረድተዋል፡፡…