- ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል ክብረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
- ኢንጂነር ታደለ ብጡል የባንክ ባለሙያ፣ ሲቪል መሀንዲስ እና ደራሲ ናቸው።
ማራዥት እና ሦስትዮሽ የተሰኙ የግጥም መድብሎች እንዲሁም የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ የአፄ ቴዎድሮስ እና የልዑል አለማሁ ቴዎድሮስን ግለ ታሪኮች ፅፈዋል። የአማርኛ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላትንም አዘጋጅተዋል።
ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍም ይታወቃሉ።
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የማታ ትምህርት ያስጀመሩ ናቸው።
በታዋቂው አርበኛ የተሰየመውን ወንዲራድ ት/ቤትን ከሌሎች ጋር በመሆን አቋቁመዋል።
የአክሱም ሀውልት ብሄራዊ አስመላሽ ኮሚቴ አባልም ነበሩ።
የተለያዩ ባህላዊ እና ትውፊታዊ ቅርሶችን ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በራሳቸው ወጪ ገዝተው በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ ሙዚየሞች በመለገስ ታሪካዊ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
የበጎ ሰው ተሸላሚው ኢንጂነር ታደለ ብጡል ክብረት በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የ2008ዓ.ም የበጎ ሰው ተሸላሚው የሀገር ባለውለታ ኢንጅነር ታደለ ብጡል በእክምና ሲረዱ ቆይተው እሑድ ነሐሴ 26 /2016ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ቀብራቸው ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2016ዓ.ም በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 6፡00ሰዓት ይከናወናል።