- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ነው
- – “ነገ ለሚድያዎች መግለጫ ስለምንሰጥ ዝርዝር መረጃ ይፋ እናደርጋለን። ከኤርትራ በኩል አየር መንገዱ ላይ የሚደረገው ጫና መጠኑ እና አይነቱ ከፍተኛ ሆኗል”- የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ወደ አስመራ የሚያደርገው በረራ ከነገ ጀምሮ ይቋረጣል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ በረራውን የሚያቋርጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር እንደሆነ ገልጿል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።
” የትኬት ገንዘብ ይመለስልን ” የሚሉ ካሉም ለቲኬታቸው ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደረግ ገልጿል።
በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።