(መሠረት ሚድያ)- ከነሐሴ 20 ጀምሮ በፋኖ ሀይሎች ተይዘው የቆዩት የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ አንተነህ መንግሥቴ እና የእቅድ ዝግጅት ዳይሬክተሩ ጋዜጠኛ ደምሳቸው ፈንታ ዛሬ ምሽት ተለቅቀዋል።
መሠረት ሚድያ በትናንትናው እለት የጋዜጠኞቹን መያዝ እና አንድ የፋኖ ሀይሎች ተወካይ ሶስቱ ግለሰቦች በቁጥጥራቸው ስር እንደሚገኙ ማረጋገጡን መረጃ አቅርቦ ነበር።
የፋኖ ሀይሎች የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ በጋዜጠኞቹ ዙርያ ማጣራት እየተደረገ እንደሆነ መናገሩን መዘገባችን ይታወሳል።
ዛሬ ምሽት ሁለቱ የአሚኮ ባልደረቦች ተለቀው ወደየቤታቸው መግባታቸውን አረጋግጠናል።