አሳዛኝ ዜና
በወላይታ የህዝብ አመፅ ተቀስቅሷል ።
ውጥረቱ ቀጥሏል። በየሀገሪቱ ክፍል መሞታችን ይብቃ !!! ለአንድነት ብለን ዝም ባልን ስቃያችን በዛ ከዚህ በኋላ የመጣውን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን። በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ ።
አዋሣ ከትላንት ጀምሮ ኔትወርክ መብራት ውሀ የለም በከተማው ውሥጥ ግልፅ ዝርፊያና ግድያ ተንሠራፍቷል። የሲዳማ ወጣቶች ወላይታዎችን እያሣደዱ በአሠቃቂ ሁኔታ እየገደሉ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የክልሉ ፖሊሶች በዝምታ እያለፉ ነው፡፡
አንድ የፌስቡክ አክቲቪስት የሚከተለውን ፅፏል ።
በሃዋሳ ዛሬም ዉጥረቱ እንቀጠለና ተኩስ እንደሚሰማ ጠዋት አንድ ሰዕት (በኢትዮጵያ) አከባቢ ያነጋገርኩት የቀድሞ የስራ ባልደረባዬ የሆነ የሃዋሳ መምህራን ኮሌጅ መምህር አሳዉቆኛል። በትላንት ዕለትም የአንድ የኮሌጁ ተማሪ አስክሬን እንዳየና በርካታ የቆሰሉ ደግሞ ወደ ሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል መጫናቸዉን አረጋግጦልኛል። የሞቱት ተማሪዎች ሶስት መሆናቸዉን የሚናገሩም አሉ። አንዱ ሟች ተማሪ የሲዳማ ዞን በንሳ አከባቢ ተወላጅ መሆኑን ጨምሮ ገልፆልኛል።
ከዚያ የጠዋት ስልክ በኻላ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና የሆስፒታል ምንጮች ጋር ብደዉልም ስልክ ሊሰራልኝ አልቻለም። በአሁኑ ሰዕት በሃዋሳ የስልክ አገልግሎት ተቋርጧል የሚል ግምት አለኝ።
ትላንትና ማምሻዉን በሃዋሳ ዩንቨርስቲ ዉጥረት እንደነበር ሰምቻለዉ። የዉጥረቱ መንስኤም ከወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ የሲዳማ ልጆች ተባረዋል ወይም ፈርተው ወተዋል የሚል ዜና ከተሰማ በሃላ መሆኑን ምንጮቼ ነግረዉኛል።
እንደሚታወቀዉ ሃዋሳ ከ ማክሰኞ ጀምሮ በ ግጭት ዉስጥ ስትሆን የሰዉ ነብስና ከፍተኛ ንብረት ጠፍቷል።
ግጭቱን የከፋ የሚያደርገዉ የብሄር ግጭት መልክ እንዲይዘ የሚሰሩ ወገኖች ከጀርባ መኖራቸዉ ነዉ። እኝህ ወገኖች በሃገር ደረጃ ለተያዘዉ