Blog Archives

ኢሕአዴግ ውሳኔውን ተከትሎ የመጡ ለውጦችን በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል።

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛው ስብሰባውን የአመለካከት አንድነትን በሚያረጋግጥና የአመራሩን አቅም በሚገነባ መልኩ ማካሄዱን ቀጥሏል። መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ነሃሴ 14/ 2010 ዓ.ም ማካሄድ የጀመረው የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጥልቅ ተሃድሶው የተላለፉ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አፈፃፀም እንዲሁም ውሳኔውን ተከትሎ የመጡ ለውጦችን በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል። ጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ እየመጡ ያሉ ሀገራዊ ለውጦች የሕዝቡን ፍላጎት በሚያሟላና ምልዓት ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ማየቱን የኢሕአዴግ የሕዝብና ውጪ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ጓድ ሳዳት ነሻ ገልፀዋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህን ሀገራዊ ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የአመለካከት አንድነት በድርጅቱ ውስጥ ሊያረጋግጥ በሚችልና የአመራሩን አቅም በሚገነባ መልኩ ውይይቱን ማካሄዱን ቀጥሏል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ከቆመበት ቀጥሏል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገመገማሉ።

ሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ከቆመበት ቀጥሏል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገመገማሉ። (ምንሊክ ሳልሳዊ) ስብሰባው ዶክተር አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ከያዙ በኋላ የመጀመሪያ መደበኛ የፓርቲ ስብሰባ ነው። ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሰረዘው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቀጣዮ ኮማንድ ፖስቱ ስራው ምን መሆን እንዳለበት ውይይት ይደረጋል ከዚህም ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሾሙ በኋላ የነበራቸው የስራ ሂደት ይገመገማል ። ኢሕአዴግ አሁን እየታየ ባለው የለውጥ ጅማሮ እየተናጠ መሆኑን ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን በቀጣይነት ወይ ይፈርሳል አሊያም የድምጹን ሂደት ያስተካክልና የሕወሃትን የበታችነት ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንዶች ኢሕአዴግን እንደ አጭበርባሪና አዘናጊ ድርጅት የሚያዩ ሲሆን በርካቶች ግን ለውጥ በመኖሩ ሂደት ላይ ይስማማሉ። የሕወሃት ሊቀመንበር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚካሔደውን ለውጥ ያላስደሰታቸው ሲሆን በተለይ የእስረኞች መፈታትና ዶክተር አብይ በአምቦ ተገኝተው ባደረጉት ንግ ግር ደስተኛ አለመሆናቸውን ከመግለጻቸውም በላይ በማሕበራዊ ድረ ገጽ ላይ ካድሬዎቻቸውን በማሰማራት የተቃውሞ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ዶክተር አብይ አምቦ ላይ በቄሮ ትግል ስልጣን ላይ ወጥተናል እናመሰግናለን ማለታቸው እስካሁን በሕወሓቶች እየታሙበት ነው። የኢሕአዴግ ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መሰረት የአብይ ደጋፊ የሚባሉት ለማ ፣ ደመቀና ገዱ ከፍተኛ የሆነ ግምገማ ይጠብቃቸዋል። ሕወሓቶች አብይ ለኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት የተመረጠበት መንገድ አብዮታዊ ዲሞክራሲን የተከተለ አይደለም በማለት ይተቻሉ። አለመተማመን እንደ ወረርሽኝ በሽታ በኢሕአዴግ ውስጥ ተስፋፍቷል። ሕወሓቶች ኦሕዴድን አብዮታዊ ዲሞክራሲንና ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን የካደ ለይስሙላ ኢሕ አዴግ ውስጥ የተሰነቀረ የከሐዲዎች ስብስብ ሲሉ ይወርፉታል። በስራ አስፈጻሚው ስብሰባ ላይ ጡረታ የወጡ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የህወሃት የደህንነት ተቋም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚን ስብሰባ መረጃዎችን “እያሾለከ” እያወጣ ነው። (ፋሲል የኔአለም)

በህወሃት ቁጥጥር ስር የሚገኘው የደህንነት ተቋም፣ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚን ስብሰባ በተመለከተ አንዳንድ መረጃዎችን “እያሾለከ” እያወጣ ነው። (ፋሲል የኔአለም) የሚለቀቁት መረጃዎች ደግሞ በለማና አብይ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። ሁለቱም ሰዎች በስብሰባው ላይ የተለዬ ተቃውሞ እንዳላሰሙ የሚያሳይ ጽሁፍ አንብቤአለሁ። ። ሽፈራው ሽጉጤም ስብሰባው ያለችግር እየተካሄደ ነው የሚል መግለጫ ሰጥቷል። በጎን ደግሞ የህወሃት ድረገጾች በእነ አብይ ላይ ያሚያደርጉትን ዘመቻ አጠናክረዋል። ህወሃት ህዝብ የሚወደውን ሰው ለማስመታት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች አንዱ፣ ሰውዬው የእሱ ደጋፊ ሳይሆን ልክ የእሱ ደጋፊ እንደሆነ አድርጎ አሉባልታ በመንዛት ነው። የህወሃትን ሴራ ሳይገነዘቡ በህወሃት አሉባልታ የሚወናበዱ ሰዎች፣ “ እሱማ ከህወሃት ጋር ይሰራል” ብለው የሚወዱትን ሰው መደገፍ ሲያቆሙና ህወሃትም የሰውዬው ህዝባዊ ድጋፍ መቀነሱን ሲያይ፣ በሰውዬው ላይ የመውጊያ ጩቤውን ይመዛል። በህወሃት አሉባልታ ህዝባዊ ድጋፉ መሸርሸሩን የተረዳው ሰው፣ ህልውናውን ለማቀዬት ሲል የህወሃት ታዛዥ ሆኖ ያገለግላል፤ አልያም ዋጋ ይከፍላል። በእነ አብይ ላይ የሚለቀቀው የፕሮፓጋንዳ አላማም ከዚህ ተለይቶ መታዬት ያለበት አይመስለኝም ፤ ሰዎቹ ከህወሃት ጋር እንደተሰለፉ አስመስሎ በማስወራት ህዝባዊ ድጋፋቸውን ለመሸርሸርና በሂደት ለመምታት ታስቦ የሚለቀቅ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ይሰማኛል። ከሚሰጡት መግለጫዎችና ጽሁፎች ተነስቼ የህወሃት የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በጥሩ መልኩ እየሄደ እንዳልሆነ መገመት እችላለሁ። እነ ለማ የትግል ስልት ለውጥ ያደረጉም ይመስለኛል ፤ በአደባባይ ብዙ ባለማውራት “ሙያ በልብ ነው” የሚለውን አገራዊ ብሂል ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ይሰማኛል። በስራ አስፈጻሚው ስብሰባ ላይም ጠንካራ አቋም ይዘው እንደቀረቡ እገምታለሁ ። ያ ባይሆን ኖሮ “አብይ እንዲህ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News