ሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ከቆመበት ቀጥሏል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገመገማሉ።

ሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ከቆመበት ቀጥሏል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገመገማሉ። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ስብሰባው ዶክተር አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ከያዙ በኋላ የመጀመሪያ መደበኛ የፓርቲ ስብሰባ ነው። ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሰረዘው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቀጣዮ ኮማንድ ፖስቱ ስራው ምን መሆን እንዳለበት ውይይት ይደረጋል ከዚህም ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሾሙ በኋላ የነበራቸው የስራ ሂደት ይገመገማል ።

ኢሕአዴግ አሁን እየታየ ባለው የለውጥ ጅማሮ እየተናጠ መሆኑን ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን በቀጣይነት ወይ ይፈርሳል አሊያም የድምጹን ሂደት ያስተካክልና የሕወሃትን የበታችነት ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንዶች ኢሕአዴግን እንደ አጭበርባሪና አዘናጊ ድርጅት የሚያዩ ሲሆን በርካቶች ግን ለውጥ በመኖሩ ሂደት ላይ ይስማማሉ። የሕወሃት ሊቀመንበር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚካሔደውን ለውጥ ያላስደሰታቸው ሲሆን በተለይ የእስረኞች መፈታትና ዶክተር አብይ በአምቦ ተገኝተው ባደረጉት ንግ ግር ደስተኛ አለመሆናቸውን ከመግለጻቸውም በላይ በማሕበራዊ ድረ ገጽ ላይ ካድሬዎቻቸውን በማሰማራት የተቃውሞ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ዶክተር አብይ አምቦ ላይ በቄሮ ትግል ስልጣን ላይ ወጥተናል እናመሰግናለን ማለታቸው እስካሁን በሕወሓቶች እየታሙበት ነው።

የኢሕአዴግ ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መሰረት የአብይ ደጋፊ የሚባሉት ለማ ፣ ደመቀና ገዱ ከፍተኛ የሆነ ግምገማ ይጠብቃቸዋል። ሕወሓቶች አብይ ለኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት የተመረጠበት መንገድ አብዮታዊ ዲሞክራሲን የተከተለ አይደለም በማለት ይተቻሉ። አለመተማመን እንደ ወረርሽኝ በሽታ በኢሕአዴግ ውስጥ ተስፋፍቷል። ሕወሓቶች ኦሕዴድን አብዮታዊ ዲሞክራሲንና ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን የካደ ለይስሙላ ኢሕ አዴግ ውስጥ የተሰነቀረ የከሐዲዎች ስብስብ ሲሉ ይወርፉታል።

በስራ አስፈጻሚው ስብሰባ ላይ ጡረታ የወጡ የወያኔ ባለስልጣናትና በቅርቡ ከስራ የተባረሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠባቂዎች ጉዳይ ለውይይት እንደሚቀርብና ሕወሓት ቁጣውን እንደሚገልጽ ታውቋል። የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልከት በተጨማሪም ከኦሮሚያና ቤንሻንጉል የሚፈናቀሉ አማሮች ጉዳይ ፤ በምስራቅ ኦሮሚያ እየዘለቀ ገብቶ ሕዝብን እየገደለ ስለሚገኘው የ አብዲ ኢሌ ልዩ የፖሊስ ሃይል ጉዳይ የውይይቱ አጀንዳ ሲሆን ኢሕ አዴግ ለነሐሴ ለሚደረገው ስብሰባ የሚያቀርባቸውን እቅዶችና ዝርዝር ጉዳዮች ወስኖ ያስቀምጣል ተብሏል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)