Blog Archives

ትግራይ ወልቃይትንና ራያን ይዤ እገነጠላለሁ ብሎ ካሰበ አማራው ዝም ብሎ አይመለከትም ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ገለፁ። (ቪድዮ)

የትግራይ ኢሌት ትግራይ ወልቃይትንና ራያን ይዤ እገነጠላለሁ ብሎ ካሰበ አማራው ዝም ብሎ አይመለከትም ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ገለፁ። (ቪድዮ) $bp("Brid_42083_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-1310727629063398.mp4", name: "ትግራይ ወልቃይትንና ራያን ይዤ እገነጠላለሁ ብሎ ካሰበ አማራው ዝም ብሎ አይመለከትም ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ገለፁ። (ቪድዮ)", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180810_064215.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የግዮን ቆይታ ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር – የኤርትራ አምባሳደርን እስከምሄድ ደረስ እንዲያገኘኝ ላኩልኝ ብዬ ለየማነ ነግሬው ነበርና አምባሳደሩ እንደሰማሁት እዛ ሰነአ ኤርፖርት ነበር።

ግዮን፡- አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንኳን ደስ ያለህ፤ እንኳን ለቤትህ አበቃህ? አንዳርጋቸው ጽጌ ፡- አመሰግናለሁ እንኳን አብሮ ደስ ያለን:: ግዮን፡- መቼና እንዴት ነበር መፈታትህን የሰማኸው? አንዳርጋቸው ጽጌ ፡- ከመፈታቴ በፊት ስድስት ሣምንት ቀደም ብሎ ቴሌቭዥን ክፍሌ ውስጥ አስገቡልኝ:: ከዛ በፊት በነበሩኝ ጊዜያት ቴሌቭዥን፣ ሬድዮም ሆነ ሌሎች የመገናኛ ብዙኃንን እንድከታተል አልፈቀዱልኝም፤ እድሉም አልተሰጠኝም ነበር። ከጠቀስኩልህ ወዲያ ግን ቴሌቭዥን ስላስገቡልኝ የወቅቱን ሁኔታ፣ የአዲሱን ጠ/ሚኒስትር መመረጥና ወደ ሥልጣን መምጣት ማወቅ የቻልኩት በዚህ አጋጣሚ ነው። ቅዳሜ ቀን ቤተሰቦቼ ሊጠይቁኝ የሚመጡት ሠባት ሠዐት ስለሆነ ከእነሱ ጋር በማደርገው ቆይታ የሠዐቱ ዜና ስለሚያመልጠኝ እስኪ የስድስት ሠዐቱ ዜና ምን ይላል? ብዬ ቴሌቭዥኑን ከፈትኩት፡ በጊዜው ዜና የለም፤ የሆነ ገፅ ዳሰሳ ነው፣ ግምገማ የሚል ፕሮግራም አለ፤ እዛ ላይ ጋዜጠኞች ከበው “ዛሬ ፌስ ቡክ (ማህበራዊ ድረ ገፅ) አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ በሚል ጥያቄ ነው የተሞላው፤ በዚህ መሠረት አቃቤ ህግ ዛሬ በጉዳዩ ላይ መልስ ሰጥቷል፤ ለአቶ አንዳርጋቸውም ይቅርታ እንደተደረገላቸው አስታውቋል” ብለው ሲናገሩ ሰማሁ። “እንዲህ ነው እንዴ?” ብዬ ነው ያዳመጥኩት። ግዮን፡- ይቅርታ እንደተደረገልህና እንደምትፈታ ስታውቅ ምን ተሰማህ? አንዳርጋቸው ጽጌ ፡- ብዙም የተለየ ስሜት አልነበረኝም፤ ዝም ብዬ ዜና እንደማድመጥ ያህል ነው የሰማሁት። እስኪ ቤተሰቦቼ ሊጠይቁኝ ሲመጡ እነሱን በደንብ እጠይቃለሁ ብዬ ተውኩት። በኋላ እነሱም የነገሩኝ ሸገር ሬድዮኖች ጉዳዩን ሰምተው ደውለውላቸው ነበር። ስለ ጉዳዩ ያውቃሉ እና አባቴ ብዙ ጊዜ ቁጭ ብሎ ነበር የሚያነጋግረኝ፤ የዛ እለት ግን ከውስጥ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሽብርተኝነት›፣ በነጻነት አዋቂው አንዳርጋቸው ተበጣጠሰ! (ቦሌ፣ ኦሎምፒያ በደስታ ተናጠች!) ( ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ )

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ‹ሽብርተኝነት›፣ በነጻነት አዋቂው አንዳርጋቸው ተበጣጠሰ! (ቦሌ፣ ኦሎምፒያ በደስታ ተናጠች!) ስለታጋዩና ፖለቲከኛው አንዳርጋቸው ጽጌ ለመጻፍ ‹‹ከየት ልጀምር?፣ ከየቱስ ጀምሬ የቱ ጋር ልቋጭ? …›› በሚለው ሀሳብ ውስጤ መናጡ አልቀረም፡፡ ስለአንዳርጋቸው የትግል እንቅስቃሴ በዝርዝር የሚያጽፉ አንኳር ርዕሠ ጉዳዮች እጅግ ብዙ መሆናቸውን አምናለሁ፡፡ የአንዳጋቸው የፖለቲካ ጉዞ ብዙ መጽሃፎችንም ያጽፋል፡፡ እኔም በዚህቺ የፍጥነት ጽሑፍ ከአንዳርጋቸው ፍቺ ጋር በተያያዘ ከባለፈው ቅዳሜ (ግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም) ጀምሮ እስከ ማክሰኞ (ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም) ድረስ በግል ባየሁትና ባስተዋልኳቸው ነገሮች ላይ ማተኮርን መረጥኩ፡፡ ዕለተ-ቅዳሜ አርብ (ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ.ም) አመሻሽ ላይ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች እንደሚፈቱ መወሰኑ በአገዛዙ ሚዲያዎች ተሰማ፡፡ ሁላችንም ደስታ ተሰማን፤ ጻፍንም፡፡ ቅዳሜ ጠዋት ረፋድ ላይ ‹‹አንዳርጋቸው ጽጌና ሌሎች ከ500 በላይ የሚሆኑ እስረኞች ተፈቱ›› የሚል ይዘት ያለው ዜና በፋና ብሮድካስቲንግ ፖርፖሬሽን ድረ-ገጽ ላይ ተነበበ፡፡ ዜናውን ወዲያው ብዙ ሰው ከሀገር ውስጥ እስከውጪ ድረስ ተቀባበሉት፡፡ ፋና ብዙም ሳይቆይ የዜናውን ርዕሥ ‹‹…እንዲፈቱ ተወሰነ›› በሚል አስተካከለው፡፡ በቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ንቁ ተሳታፊ በነበረውና አሁንም በማኅበራዊ ሚዲያ በድፍረት ሀሳቡን በሚያራምደው ስንታየሁ ቸኮል የተመራው ግብረ ሀይል ወደቃሊቲ ገሰገሰ፡፡ ስንታየሁ ቃሊቲ አከባቢ ስላሉ መረጃዎች በፍጥነት ያደርሰን ነበር፡፡ እኔና እሱም በስልክ መረጃዎችን ስንለዋወጥ ነበር፡፡ ከሰዓት በኋላ፣ የአንዳርጋቸው ጽጌ ወላጅ አባት አቶ ጽጌ ሀ/ማርያም ወደቃሊቲ እስር ቤት አምርተው ወደውስጥ በመግባት ስለልጃቸው ፍቺ ጠየቁ፡፡ የቃሊቲ እስር ቤት ሃላፊዎችም ‹‹እኛው
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከአንዳርጋቸው ጀርባ ፤ (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

ከአንዳርጋቸው ጀርባ……… (ብርሀኑ ተክለያሬድ) “በልጅነቴ አንድ ሰው አባቴን ፍለጋ ቤት ይመጣል ይህ ሰው አባቴን ፍለጋ የመጣው አንድ ጉዳይ እንዲፈፅምለት ጉቦ ሊሰጠው ነበር የገንዘቡ መጠን 10.000ብር ነበር ያ ገንዘብ በኛ የልጅነት ዘመን ምን ያህል ብዙ እንደነበር ሳስብ ይገርመኛል አባቴ ሰውየው የመጣበትን ምክንያት እንዳወቀ ወደ ቤት ገብቶ ሽጉጥ ይዞ ወጣ እናታችን ደንግጣ አባቴን መለመን ጀመረች አባታችን ደግሞ እንዴት ጉቦ ልስጥህ ይለኛል ብሎ ሰውየውን ለመግደል ተገለገለ በመጨረሻ በእናታችን ልመና ሰውየው ገንዘቡን ይዞ ከግቢያችን ተባረረ ይህን ካየሁ ቀን ጀምሮ የገንዘብ ፍላጎቴ ጠፋ የኔ ያልሆነ ገንዘብ ላለማጥፋት መጠንቀቅ ጀመርኩ ለዛም ነው የአዲስ አበባን መሬት አላዘርፍም ብዬ ከነ ታምራት ላይኔ ጋር የተጣላሁት ለዛም ነው የድርጅቴን 400ዶላር አላጠፋም ብዬ ለመያዝ የበቃሁት አባቴ ያሳደረብኝ በጎ ተፅእኖ ቀላል አይደለም” ይህ ታሪክ ታላቁ ሰው አንዳርጋቸው በፍቺው ማግስት ስለቤተሰቡ ስጠይቀው የነገረኝ ነው ከታላቁ ሰው ጀርባ ብዙ በጎ ተፅእኖ ያሳረፉበት ዛሬም በፅናት ቆሞ እናገኘው ዘንድ የለፉ መልካም ቤተሰቦች አሉት አባቱ አቶ ፅጌ ሀብተማርያም ከላይ ካለው ታሪክ በላይ በአንዳርጋቸው ህይወት ውስጥ እስከዛሬ ድረስ ትልቁን የአባትነት ሚና ሲወጡ ኖረዋል የሱ አባት መሆናቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በእርጅና ዘመናቸው በወሮበላ መንግስት ነኝ ባይ ታፍነው ለ3 አመታት ታስረዋል ከተፈቱ በኋላም በማረፊያቸው ጊዜ ልጃቸውን ለ4 አመታት ከባለቤታቸው ጋር ብቻ እንዲጠይቁ እዳ ተጥሎባቸዋል ጋሽ ፅጌ የማይለካ ምስጋና ከአንዳርጋቸው ወዳጆች ይገባቸዋል እህቶቹ እስከዳርና አይኔ የዚሁ ተፅእኖ ውጤቶች ናቸው አንዳርጋቸውን ለመቀበል
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ትናንት አንዳርጋቸውን አግኝቸው ነበር፤ልጆቹን ሰላም በልልኝ አለኝ፤እሽ አልኩትና በኋላ ግን አላቀስኩ” አርበኛ ዘመነ ካሴ

<<ትናንት አግኝቸው ነበር፤ልጆቹን ሰላም በልልኝ አለኝ፤እሽ አልኩትና በኋላ ግን አላቀስኩ>> አርበኛ ዘመነ ካሴ ከአንዳርጋቸው መፈታት ማግስት ስለነበረው የስልክ ልውውጥ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መፈታት ተከትሎ ሰዎች ምን ስሜት ይሰማቸው ይሆን? ብየ ሳስብ ከቤተሰቦቹ ቀጥሎ ቀድሞ የመጣልኝ የበረሃ የትግል አጋሩ ያን ጊዜ ክፉ ደጉን አብሮ የተጋራው አርበኛ ዘመነ ካሴ ነበር።እናም ዘሜን ምን ይሰማው ይሆን ብየ በቀጥታ ስጠይቀው እንዲህ ነው ያለኝ። <<…. ትናንት አግኝቼው ነበር።እና የት እንዳለሁ እንኳን አያውቅም።ሌሎችን ልጆች ሰላም በልልኝ አለኝ።እሽ አልሁት።በኋላ ግን አለቀስሁ።>> ቀሪ መልዕክቶቹን ለራሱም ይሁን ለህዝብ ጊዜው ሲደርስ ይግለፃቸው በሚል ስሜቱን ብቻ ነው ሳልሸራርፍ ያደረስኳችሁ። ዘመነ ውስጡ ታፍኖ ስሜቱን መግለፅ የሚችልበት እድል ስላጣ ሳይሆን ሁኔታዎች ስላልፈቀዱ በፈጣሪ እና በሰዎች ትግል የሚኖር ነው።እንደ አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ ባይወድቅም ከአውሬ ጉሮሮ የተረፈ፤ነገር ግን በትግሉ ውስጥ ለመሳተፍ አሁንም ሁኔታዎች ያልፈቀዱለት ወንድማችን ነው። እናም ዘሜ ያንን የበረሃ ጓዱን፣ውሃ አብሮት የሚቀዳውን፣ስፖርት አብሮት የሚሰራውን፣እንጨት አብሮት የሚፈልጠውን፣የበረሃ ትጥቅ ትግል ቅልስ አብሮት የቀለሰውንና በኋላ ግን በጠላት እጅ ወድቆ በፈጣሪ ሀይል ከጠላት እጅ የወጣውን አንዳርጋቸውን ሲያገኘው በሁለት ስሜት እየተላጋ እምባ ማንባቱ ሌሎቻችንም ልባችን የሚሰብር መሆኑ ይታወቃል።እኔ በግሌ ሲስቅና ሲጫወት የማውቀው አንደበተ ርዕቱ እና ልበሙሉው ዘሜ ይህንንና መሰል “ጥቂት ጉዳዮችን” ሲያጫውተኝ መቋቋም የማልችለው ስሜት ውስጥ ነበርኩ። ነገ ዘሜ እና አንዳርጋቸው የትና በምን ሁኔታ እንደሚገናኙ ሁኔታዎች የሚያሳውቁን ሁኖ ለጊዜው ግን ቢያንስ በጋራ ስሜታቸውን መጋራት በመቻላቸው እጅጉን ደስ ብሎኛል። ጨዋታው የማይሰለቸው
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከናሁ ቴሌቪዥን ቃር ያደረገውን ቆይታ ይመልከቱ።

  አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከናሁ ቴሌቪዥን ቃር ያደረገውን ቆይታ ይመልከቱ። $bp("Brid_17684_2", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://www.mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/Facebook-1757497637691341.mp4", name: "አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከናሁ ቴሌቪዥን ቃር ያደረገውን ቆይታ ይመልከቱ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/IMG_20180601_085655.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

በለንደን የሚኖሩት የአንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ከቢቢሲ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

  በለንደን የሚኖሩት የአንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ከቢቢሲ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ $bp("Brid_17435_3", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://www.mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/05/የአንዳርጋቸው-ጽጌ-ቤተሰቦች-ከቢቢሲ-ጋር-ያደረጉት-ቃለ-ምልልስ.mp4", name: "በለንደን የሚኖሩት የአንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ከቢቢሲ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/05/Free-andargachew-Tsige-2018-may-10.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው እስከ ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

(የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው) እስከ ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። ይህ ለፖለቲከኞች ብቻ የማይተው የዜጎች ቀጣይ ተግባር ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሰከነና በሰለጠነ መንገድ መልካም ጅማሮዎች ሊበረታቱ ይገባሉ፤ ነገ ሊያስከትሉ የሚችሉት ጥሩና መጥፎ ነገሮችንም በሰከነ መልኩ አትኩሮት ሰጥቶ ማሰብ ለዘላቂ ስኬት መሰረት ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያላየነውን ጭላንጭል እያየን ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከነበረው አስተዳደር ያተረፍነው ነገር ሞት እስር ስደትና መከራ ነው። ( ፖለቲካው በሴራ እስካልተያዘ ) ድረስ የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ አይወስድም ። ዶክተር አብይ አሕመድ መልካም ነገሮችን ለሕዝብ በማሳየት ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል። በቀጣይነት ደግሞ የኛ ተግባር መሆን ያለበት እየታዩ ያሉ መልካም ጅማሮዎች እንዳይከሽፉ በትግላችን ማረጋገጥ ነው። የዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ብሔራዊ እርቅ የሚደረገውን መንገድ መጥረግም የዚህ መልካም ነገር አካል መሆኑ እያየን ነው። በጥንቃቄና በታታሪነት ሊያዝ የሚገባው የመልካም ፖለቲካ ጅማሮ ሕዝቦች በሃገራቸውና በመንግስታቸው እንዲተማመኑ በሩን ይከፍታል። የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው እስከ ፍንጭ እስካሳየው ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። ፈጥኖ ከማጨብጨብ ይልቅ ፈጥኖ ማበረታታትና የተገኘው ድል እንዳይከሽፍ ከእያንዳንዱ የሰላም ሰው ጎን መቆም ያስፈልጋል። ይህ ሲባል ጎን ለጎንም መልካም ጅማሮዎችን ለማክሸፍ የሚራወጡ እኩያንን እየቀበሩ መሆን ይገባዋል። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያላየነውን ጭላንጭል እያየን ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከነበረው አስተዳደር ያተረፍነው ነገር ሞት እስር ስደትና መከራ ነው። አሁን ግን እነዚህ ስቃዮች በትንታግ የሕዝብ ትግሎች ፈር እየያዙ መልካምነትና ቅንነትን እየደመሩ መስመር ውስጥ ገብተዋል። እነዚህን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተወያዩ

“ጥሩ ነገር እስከሰሩ ድረስ እኛ የመቃወም ሱስ የለብንም። ጠ/ሚኒስትር አብይ ከህዝብ ጋር ያደረጋቸውን የተለያዩ ውይይቶችን ተከታትያለሁ ጥሩ ጅምር ነው። ተስፋ የሚሰጥ ነገር ይታያል።” – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የግንቦት ሰባት ፓርቲ ጸሃፊ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበር ከሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውንና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት የገለጹ ሲሆን በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

Video : በቶሮንቶ የሚኖሩ ኢትዬጵያውያኖች ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የደስታ መልእክት አስተላለፉ።

Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ለዚህ ቀን መምጣት ለደከሙት… ለሁሉም ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ (አንዳርጋቸው ፅጌ) (ቪድዮ)

Andargachew Tsige Public Speech (ቪድዮ) ‹ብዙ ሰው እንደሚጨነቅ ብዙ ካምፔይን እንደሚደረግ መረጃ ባይኖረኝም እጠረጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን ዝምብለው እንደማይተኙ አቃለሁ፡፡ እዚህ ያየሁት ዓይነት አቀባበል ግን ፈጽሞ ይሆናል ብይ ያላሰብኩት፣ ያላለምኩት ነገር ነው፡፡ በዝርዝር መሄድ አልችልም፡፡ ለዚህ ቀን መምጣት ለደከሙት… ለሁሉም ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ በዚህ አራት ዓመት የተከፈለው መስዋዕትነት (እስራቱ) እኔ በበኩሌ ‹በጣም ትንሽ ነው› ነው የምለው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገብቶበት ከሚገኘው አሰቸጋሪ ሁኔታ አራት ዓመት አይደለም፤ ለደህንነት ደጋግሜ ነግሬዋለሁ፤ እንዲህ ዓይነት አገር ከማየት ፍርድ ቤታችሁ የወሰነውን የሞት ፍርድ ፈርዳችሁ እንድትገሉኝ ነው ያልኩት፡፡ ቆራርጠው በቴሌቪዥን ያቀረቡትን ሰምቻለሁ፤ ዛሬ እዚህ ተቀምጨ እደግመዋለሁ፤ ያቀረብኩት ጥያቄ ፍርድ ቤታቸው ያስተላለፈውን የሞት ፍርድ በአስቸኳይ እንዲፈጽሙ፤ ሰው እየሳቀ ለመብቱም ለሕዝቡም መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁያልኩት፡፡ እንደ እነ ለገሰ አስፋው ፍቱኝ አልላችሁም፡፡ በ83 እሰከ 85 አገልግያችኋለሁ፤ ያንን ውለታ ቆጠራችሁ የሞት ፍርዱን ተፈጻሚ ታደርጋላችሁ ነው ያልኳቸው፡፡››
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከቤተሰባቸው ቤት መልእክት አስተላለፉ ።

Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ግንቦት 20 ኢሕአዴግ አንቀጠቀጥኩ የሚለው ተራራ በአንዳርጋቸው ጽጌ ፈርሶ እርቃኑን ቀርቷል !!!

ግንቦት 20 ኢሕአዴግ አንቀጠቀጥኩ የሚለው ተራራ በአንዳርጋቸው ጽጌ ፈርሶ እርቃኑን ቀርቷል !!! (ምንሊክ ሳልሳዊ) አንዳርጋቸው ጽጌን ለምን መደበቅ አስፈለገ ?? አንዳርጋቸው ላይ የደረሰ የ አካልና የሞራል ጉዳት ሁሉ ተጠያቂው ኢሕአዴግ ብቻ ነው። ተራራ አንቀጠቀጥኩ የሚለው ኢሕአዴግ እና ሊቀመንበሩ አንዳርጋቸው ፅጌ ሕዝብ እንዳያየው ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጋር ባደረጉት ድርድር ኤምባሲው ጊቤ ውስጥ ቆይታ እንዲያደርግ ሆኗል። ከእስር ሲፈታ ቪዛ ስላሌለው ቀጥታ የኢሕአዴግ መንግስት ወደ ለንደን እንደሚመልሰው በተለያየ መንገድ ባለፉት ቀናት ሲናገር ተደምጧል። በተናገረው መሰረትም ተግብሮታል። የእንግሊዝ አምባሳደር የኢሕአዴግን ጠቅላይ ሚኒስትር ባናገሩበት ወቅት በአንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የኢሕአዴግ አቋም እንደማይለወጥ ተነግሯቸዋል። የንግ ግር ዋናው ነጥብ የነበረው አንዳርጋቸውን መፍታት ሳይሆን አንዳርጋቸው የሚፈታበትና በቀጣይነት የሚሆነው ተግባር ነበር። በገፅታ ግንባታ ላይ የተሰማሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዳርጋቸውን በቢሯቸው ተቀብለው ያነጋገሩት ያህልም ፕሮፓጋንዳ እንዲነዛ አድርገዋል። ከቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ ጋር እንዳይገናኝ ትልቅ ጋሬጣ የሆነው ኢሕአዴግ ከእንግሊዝ ዲፕሎማቶች እግር እግር ስር በማለት አንዳርጋቸው አጠገብ ማንም ኢትዮጵያዊ እንዳይጠጋ ትልቅ እንቅፋት ሲሆኑ ተስተውለዋል። ግንቦት 20 በዲሞክራሲ ሽፋን የዘረኝነት ፣ የጥላቻ ፣ የግለኝነት ፣ የዘረፋ ፣ የድህነት ፣ የድንቁርና ፣ የግድያና የእስር ምዕራፍ የተከፈተበት እኩይ ቀን ነው።ግንቦት ሐያ ኢሕአዴግ አንቀጠቀጥኩ የሚለው ተራራ ፈርሶ እርቃኑን ቀርቷል። ኢሕአዴግ ራሱን የሚያወዳድረው ከራሱ እቅድ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ሳይሆን ከሞቱ እና ከተቀበሩ ጨቋኝ ገዢዎች ጋር መሆኑን የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ራሱ ወያኔ ጨቋኝ አምባገነን መሆኑን ብቻ ነው። በሙስና ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ባለስልጣናቱን ኢሕአዴግ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ፅጌ ከቃሊቲ እስር ቤት የወጣ ሲሆን ቤተሰቦቹን ከተገናኘ በኃላ ወደ ለንደን ይበራል ።

አንዳርጋቸው ፅጌ ከቃሊቲ እስር ቤት የወጣ ሲሆን ቤተሰቦቹን ከተገናኘ በኃላ ወደ ለንደን ይበራል ። የአንዳርጋቸው ፅጌ ቤተሰቦች አንዳርጋቸው በማንኛው ስዓት ሊመጣ ስለሚችል ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ መባላቸው ታውቋል። #MinilikSalsawi አንዳርጋቸው ፅጌ ከቃሊቲ እስር ቤት የወጣ ሲሆን ቤተሰቦቹን ከተገናኘ በኃላ ወደ ለንደን ይበራል ።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ጽጌን ለመውሰድ የብርቲሽ ኢምባሲ መኪኖችን ይዘው ቃሊቲ መጥተዋል መንገድ ተዘግቷል።

የብርቲሽ ኢምባሲ መኪኖችን ይዘው መጥተዋል አንዳርጋቸው ጽጌን ሊወጣ ነዉ:: መንገድ ተዘግቷል። ቃሊቲ በዋናዉ በር በኩል የሚያልፉ መኪኖች ጥግ እንዲይዙ እየተደረገ ነዉ በአካባቢዉ ያሉ ሰዎች በሙሉ አስነስተዋቸዋል ዙሪያዉ የፀጥታ ኀይሎች እየከበቡ ነዉ::      
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር ተፈቶ በሁለት ቀናት ውስጥ ለንደን እንደሚገባ የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ ።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ከሰአታት በፊት ለአንዳርጋቸው ባለቤት የሚ ሃ/ማርያም ስልክ ደውለው አንዳርጋቸው ከእስር ተፈቶ በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ለንደን እንደሚገባ ነግረዋታል። Sky news የዘገበውን ተመልከቱ $bp("Brid_16357_4", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://www.mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/05/Facebook-2157505504469399.mp4", name: "አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር ተፈቶ በሁለት ቀናት ውስጥ ለንደን እንደሚገባ የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/05/Free-andargachew-Tsige-2018-may-10.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ከሰአታት በፊት ለአንዳርጋቸው ባለቤት የሚ ሃ/ማርያም ስልክ ደውለው አንዳርጋቸው ከእስር ተፈቶ በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ለንደን እንደሚገባ ነግረዋታል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ታላቁን ሰውዬ ያልፈቱት ለምን ይሆን ?! — ” ..በነገው እለት የእንግሊዝ ኢምባሲ………”

ታላቁን ሰውዬ ያልፈቱት ለምን ይሆን ?! — ” ..በነገው እለት የእንግሊዝ ኢምባሲ………” — አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ የቀረበውን የምህረት ጥያቄ ፤ ፕሬዚዳንት ሙላቱ በመቀበል ፈርመው ወደ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንደላኩ ፤ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ እንደገለጸው ከሆነ ” አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ 745 ታሳሪዎች በልዩ ሁኔታ በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኖል” በማለት መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ግን ይህ መረጃ ይፋ እስከሆነበት ሰዓት ድረስ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር አልተፈቱም ወይም ያሉበት ሁኔታ ምን እንደሆነ አይታወቅም ። “መንግስት” በግልጽ ለሕዝብ የገባውን ቃል እስካሁን መፈጸም አልቻለም ፤ የአንዳርጋቸው ፅጌ አባት ፣ አቶ ፅጌ ሀብተማርያምን ጨምሮ ዘመድ ወዳጅ በውጪ እንዲሁም በሃገር ውስጥ ያሉ የቅርብ ሰዎች አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሚገኙበት ሁኔታ ምን እንደሆነ ለማወቅ አልተቻላቸውም ፤ ጉዳይን አስመልክቶ “በመንግስት” ወይም በአሳሪዎቹ በኩል ለማወቅ የተደረገው ጥረት ሁሉ አልተሳካም ። ይህ በእንዲህ እንዳላ በትላንትናው እለት (ቅዳሜ) ግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የገቢዎች እና ጉምሩክ ዳይሬክተር የነበረቱ አቶ መላኩ ፋንታ ፣አቶ ገብረዋሀድ ጨምሮ ከቃሊቲ እስር ቤት ከእስር የተፈቱ ሲሆን፤ ዛሬ (እሁድ) ግንቦት 19 ቀን 2010 ዓ.ምበተመሳሳይ መልኩ ከዚሁ እስር ቤት ጠዋታ ታሳሪዎች መፈታታቸው ለማወቅ ተችሏል ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ “መንግስት” አቶ አንዳርጋቸው ከእስር ቤት አውጥቶ አዲስ አበባ እንግሊዝ ኢምባሲ እንዳስገባቸው ፣ እንዲሁም ወደ ሃገር እንግሊዝ እንደላካቸው በሰፊው እየተወራ ወይም በብዙዎች ዘንድ እየተገመተ ነው። ዛሬ ከሰዓት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ጽጌ በሚቀጥለው ሳምንት ይፈታል ሲሉ ጠ/ሚ አብይ ተናገሩ

ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ትላንትና ማታ በቤተመንግስት በተደረገ የእራት ግብዣ ላይ ዶ/ር አብይ አህመድ በቀጣዩ ሳምንት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንፈታለን ማለታቸውን ፅፏል። “አቶ አንዳርጋቸውን በማሰራችን የተጠቀምነው ነገር የለም። የተረፈን ጥላቻና ከእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊዮን ዶላር ማጣታችን ብቻ ነው።” ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ትናንት ምሽት በቤተመንግስቱ የእራት ግብዣ ላይ ከተናገሩት።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከእስር ለመፍታት ተወስኖ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የተመራ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው

በእስርና እንግልት ላይ የነበረውን የአርበኞች ግንቦት ስባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከእስር ለመፍታት ተወስኖ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የተመራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ። መረጃውን ለዋዜማ ያደረሱና ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደነገሩን አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈታ ውሳኔ ከተላለፈ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል። በቅርቡ ከእስር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል። አንድ የፍትሕ ሚንስቴር ባልደረባ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ጉዳዩ በመስሪያ ቤታቸው አካባቢ መነጋገሪያ እንደነበርና ጉዳዩ በከፍተኛ ባለሥልጣናት በኩል በምስጢር ተይዞ ቆይቷል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ሲፈታ በቀጣይ በሚኖራቸው የፖለቲካ ሚና ላይ ንግግር መደረግ አለበት ብለው የሚያምኑ ወገኖች እንዳሉ የነገሩን እኚሁ ግለሰብ በማረሚያ ቤቶች፣ በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ፣ ግንባሩ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ብድኖች እና በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት መካከል መግባባት ለመፍጠር እየተሞከረ መሆኑን መስማታቸውን ነግረውናል። በአንዳርጋቸው ጉዳይ በአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች መካከል ስለነበረ ውይይት ብዙ የተሰማ ነገር የለም። ይሁንና ብአዴን የሚደርስበትን የሕዝብ ጫና ለማስታገስ የአንዳርጋቸውን መለቀቅ ሳይገፋፋ እንዳልቀረ ይገመታል። ስለጉዳዩ ከአንዳርጋቸው ቤተሰቦችም ሆነ ከአርበኞች ግንቦት 7 እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ወሬው ባለፉት 3 ቀናት በስፋት መሰማት የጀመረው ውሳኔውን በተለያየ ደረጃ ያሉ ሰዎች እንዲያውቁት በመደረጉ ሊሆን እንደሚችል የዋዜማ ምንጮች ተናግረዋል። የአቶ አንዳርጋቸው መፈታት በድርጅታቸው፣ አልፎም በአገሪቱ ፖለቲካ አቅጣጫ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ ብዙዎች በቅርበት የሚከታተሉት ጉዳይ ይሆናል። አቶ አበእስርና እንግልት ላይ የነበረውን የአርበኞች ግንቦት ስባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከእስር ለመፍታት ተወስኖ በጠቅላይ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብርቱዋን ሴት ወ/ሮ የምስራች ኃ/ማርያም – የታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ባለቤት

ስለ አንዳርጋቸው ስናወሳ ብርቱዋን ባለቤቱን ወ/ሮ የምስራች ኃ/ማርያምን ማንሳት ፣ማመስገን ፣ማድነቅ ተገቢ ነው ፨ ይህች ድንቅ ሴት አንዳርጋቸው ለእኛ ሲሟገት ከባዱን የቤተሰብ ሃላፊነት ለመሸከም የፈቀደችው ህልሙን ስለምትጋራ ነው! ለነፍስ ጥምረት አንዳርጋቸውን ስትፈቅድ ገና ማንነቷ እዛ ውስጥ አለ ፤ራመድ ያለ ብቻ ራመድ ካለ ሰው ጋር ይጣመራል፨ በአንዲ ውስጥ የምስራችን በእሷ ውስጥ እሱን ማየት ይቻላል፨ አንዳርጋቸው ከተያዘ ጀምሮ ልጆችን ከማረጋጋት ጀምሮ ብቸኛ ወላጅ መሆን ከባድ ነው! የሚ ግን ችላለች ፤በአደባባይ ስታወራ የቤት ሸክሟን አንስታ አታለቃቅስም፤ በርትታ ታበረታለች እንጅ! ብርቱዋ ሴት እናከብርሻለን ፣ህመምሽ ይሰማናል ፣ቁስልሽ ይጠዘጥዘናል ፤ አብረን የምንስቅበት ቀን ግን ይመጣል !!!!!እድሜና ጤና ከነመላው ቤተሰብሽ !!!!!
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸዉ ጽጌና ታምራት ላይኔ! (ከስንትአየሁ ባይኔ)

አንዳርጋቸዉ ጽጌና ታምራት ላይኔ! (ከስንትአየሁ ባይኔ) ሰሞኑን ስለ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በፌስቡክ መንደር ብዙ እየተባለ ነዉ፡፡ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌን በአካልም ሆነ በሌላ መንገድ አላዉቃቸዉም፡፡ የደረሰባቸዉ ሁኔታ ግን እጅግ ያሳዝነኛል፡፡ ምስላቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ምንትያ ልጆቹን ስመለከት በእዉነት የሚሰማኝን የሃዘን ስሜት በቃላት መግለጽ አልችልም፡፡ አቶ አንዳርጋቸዉ መያዛቸዉን ስሰማ ግንቦት ሰባት አለቀለት ነበር ያልኩት፡፡ ይለቅለት አይለቅለት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸዉ የሚያዉቁት፡፡ ለማንኛዉም አቶ አንዳርጋቸዉን አንድ ጊዜ ብቻ የያኔዉ ኢህዴን የዛሬዉ ብአዴን በጠራዉ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ እግር ጥሎኝ በርቀት የማየት ዕድል ገጥሞኝ ነበር፡፡ ወሩ የካቲት ይሁን መጋቢት ቢምታታብኝም ዘመኑ ግን 1985 ዓ/ም ነበር፡፡ እና ስለ አንዳርጋቸዉ የሆነ ነገር በተባለ ቁጥር ትዝ የሚለኝ በዚያ ኮንፈረንስ በአቶ ታምራት ላይኔና በእሳቸዉ መካከል ተፈጥሮ የነበረዉ ዱላ ቀረሽ የሃሳብ ጦርነት ነዉ፡፡ ነገሩ የሆነዉ እንዲህ ነበር፡፡ የያኔዉ ኢህዴን ድርጅታዊ ኮንፈረንስ የጠራዉ ጦሳ ስር በከተመችዉ ደሴ፣ ሆጤን ተንተርሶ በተገነባዉ ወሎ የባህል አምባ አዳራሽ ዉስጥ ነበር፡፡ የስብሰባ አደራሹ ከህዝብ ስራና ከኢህዴን ሰራዊት በመጡ ተሳታፊዎች ጢም ብሏል፡፡ ሁሌም ከመድረክ የማይጠፉት “ጓዶቻችንና እንዳያልፉት የለም” የሚሉት የኢህዴን መዝሙሮች ሲዘመሩ ወቅቱ በታጋይነትና በመንግስትነት መካከል የመዋለል (አዲስ ጥገኛ ገዥ መደብ በመሆንና ባለመሆን መካከል) ሁኔታ ስለነበር ለፍትህና ለእኩልነት ቅርብ የሆነዉ ታጋይ በተደበላለቀ ስሜት ዉስጥ ሆኖ ነበር የተከታተለዉ፡፡ ነገሮች በፍጥነት እየተበላሹ ስለነበር ለዚህ ለዚህስ ደርግ ባልወደቀ ይሻል ነበር በሚል ስሜት ተዉጠዉ የሚያነቡም ነበሩ፡፡ የመክፈቻዉ ዝግጅት ማታ ተጠናቆ በሚቀጥለዉ ቀን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ጽጌ

አንዳርጋቸው ጽጌ ( ታደሰ ብሩ ኬ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ይበልጥ ባወቅሁት መጠን ይበልጥ እያከበርኩትና እያደነቅሁት የሄደ ወዳጄ፣ ጓዴና መሪዬ ነው። ለብዙዎች መሪዎች ከባድ የሆኑ አጣብቂኖችን (የአመራር ወለፈንዲዎች) አቻችሎ መምራት የቻለ ሰው ነው። አንዳንዶችን ልጥቀስ 1. ለውጥ እና ሥርዓት ጥሩ መሪ የለውጥ ሃዋሪያ ነው። ለለውጥ ያልተነሳሳ ሰው መሪ መሆን አይችልም። ለውጥ ደግሞ ነባር ህጎችንና ልማዶችን መቃወም እና በአዳዲስ ህጎችና ልማዶች እንዲተኩ መጣር ይጠይቃል። ለውጥ ማፍረስን ይጠይቃል። በአንፃሩ፣ መሪ ህግን አክባሪ ነው፤ ባህል አክባሪ ነው። መሪ ያላከበረው ህግ መቸም ቢሆን ሊከበር አይችልም። ልማዶችንም ማክበር ከጥሩ መሪ የሚጠበቅ ተግባር ነው። መሪ የሥርዓት ምንጭ ነው። አንዳርጋቸው የለውጥ መሪ ነው። ሁሌ አዳዲስ አሰራሮች መሞከር ይወዳል፤ አዳዲስ ሀሳቦችን ያመነጫል። ለውጥ በአገር ብቻ ሳይሆን በድርጅት ደረጃም እንዲኖር ይፈልጋል። በአንፃሩ ደግሞ ሥርዓት ያጠብቃል። ለምሳሌ ጠዋት የመጀሪያ ሥራዉ በዕለቱ የሚሠሩ ሥራዎችን ዝርዝር (To do list ) ማዘጋጀት ነው። ከትናትናው ያደሩትን ወደዛሬ ያሸጋግራል፤ የዛሬዎችን ይጽፋል፤ ትናንሽ ነገሮችን ሳይቀር ይመዘግባል፤ ተራ የሚባል ነገር እንኳን – ለምሳሌ ኢሜሎችን ከፍቶ ማየት – በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል። አንዳርጋቸው ራሱን በሥርዓት ገድቦ የሚመራ ሰው ነው፤ በዚያው መጠን ደግሞ የለውጥ አቀንቃኝ ነው። ይህ ባህርዩ በሌሎች ብዙ ነገሮች ይገለፃል። የለውጥ ሀሳብ ያመነጫል፤ ወዲያው ደግሞ ከለውጥ በኋላ ስለሚኖረው ሥርዓት ይጨነቃል። 2. መምሰል እና መለየት ጥሩ መሪ ተከታዮችን መምሰል አለበት። ተከታዮች ሲራቡ መራብ፤ ሲታረዙ መታረዝ አለበት። ተከታዮች የሚሠሩትን ሥራ እሱም
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ፅጌ ለሐቅ የቆመ የሕዝብ ልጅ ዛሬም ስሙ ወያኔን ያስቃዣታል ።

አንዳርጋቸው ጽጌ የአዲሥ አበባ ልጅ ነው። ገና በአፍላ እድሜው አሲምባ በተባለ የትግራይ ተራራ የመሸገውን የኢህአፓን ጦር (ኢህአሠን) ተቀላቀለ። ኢህአፓ በወያኔ ተመትቶ ሲበታተን አንዳርጋቸው ጽጌ ቆሥሎ ተያዘ። ወያኔ የአማረኛ አሥተርጓሚ ድርጅት ትፈልግ ነበርና አንዳርጋቸውን በአንድ ገበሬ ቤት አሥቀምጣ ማህተም አሥቀርጻ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ንቅናቄ (ኢህአን) የተባለ ድርጅት እንዲመሠርት አደረገችው። አንዲ ከአንድ ጓደኛው ጋር ሆኖ የተባለውን ድርጅት መሠረተ። አንዳርጋቸው ቁሥሉ ሲያገግምለት ድርጅቱን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎት በሡዳን በኩል አድርጎ እንግሊዝ ሀገር ከተመ። ጓደኛውም በሡዳን ቀልጦ ቀረ። ወያኔ የፈለገችው የአማረኛ አሥተርጓሚ ድርጅት ውሃ በላው። ከዚህ በኋላ ወያኔ ሌላ ታዛዥ ፍለጋ አይኗን እነ በረከት ሥምኦን ላይ አሣረፈች። በረከት፣ አዲሡ፣ ህላዌ፣ ታምራት፣ ያሬድ… ሆነው ኢህዴን የተባለ የህወሃት የአማርኛ ዲፓርትመን ከፈቱ። ህወሃትን መንገድ እየመሩ አዲሥ አበባ ሲገቡ የቀድሞው የኢህአፓ ጓዳቸውን አንዳርጋቸውን ከእንግሊዝ ሀገር አሥመጡት። የኢህዴን ማዕከላዊ ኮሜና አባልና የአዲሥ አበባ መዘጋጃ ቤት ዋና ጸኃፊም አደረጉት። አንዲ ተራ ሠው አይደለም። እንደነ በረከት ሥምኦን፣ አዲሡና ታምራት የተባለውን ሁሉ እሽ ብሎ የሚቀበል ሠው አልነበረም። በ1985 ክረምት ላይ ኢህዴን በደሴ ከተማ ከነባር ታጋዮች ጋር ሥብሠባ አደረገ። በዚህ ሥብሠባ ላይ የህወሃትን የበላይነት ከሞገቱ ሠዎች ውሥጥ አንዳርጋቸው አንዱ ነው። ህወሃት ለምን ሁሉን ነገር ጠቅልሎ ይይዛል ሲሉ እነ ታምራት ላይኔን አፋጠው ያዙ። ጀኔራል ተፈራ ማሞ በቅርቡ ከጊወን መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልሥ እንደነገሩን ታምራት ላይኔ ለተጠየቀው ጥያቄ የሠጠው መልሥ አሳፋሪ ብቻ ሣይሆን አሥቂኝም
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ጽጌ ልዩ የኢትዮጵያ አፈር – (ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ)በድምፅ

Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዶ/ር አብይ ቀናኢነትና የአንድነት ኃይሉ ማፈግፈግ; ስለአንዳርጋቸው መጮህና ምፀቱ! (በመሃመድ አሊ )

(በመሃመድ አሊ ) የአል-በሽር ምላሽና አንደምታው; የዶ/ር አብይ ቀናኢነትና የአንድነት ኃይሉ ማፈግፈግ; ስለአንዳርጋቸው መጮህና ምፀቱ! “የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች እንዲለቀቁ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ኢትዮጵያዊያኑ እንዲፈቱ ወሰኑ” ይህ ዜና በሁሉም ብዙሃን መገናኛዎች እየናኘ ሲሆን ድብቅልቅ ያለ ስሜት ፈጥሮብኛል። በአንድ በኩል ከቤተሰብና ከዘመድ ርቀው በሰው አገር እሥር ቤት ሲማቅቁ የነበሩ ወገኖቻችን በመፈታታቸው ተደስቻለሁ። ዶ/ር አብይ አህመድም ከተለመደው ዲፕሎማሲያዊ የቃላት ጨዋታ ባለፈ በእሥር ላይ ለነበሩ ወገኖቻችን ትኩረት ሰጥተው ጥያቄውን ማቅረባቸው; እንዲሁም የሱዳኑ ፕሬዝዴንት ሀሰን ዑመር አልበሽር ጥያቄውን ተቀብለው አፋጣኝ ውሳኔ መስጠታቸው አስደምሞኛል። በርግጥ የሱዳን መንግሥት ቀደም ብሎ በሀገሩ ያሠራቸውን የፖለቲካ እስረኞች ሙሉ በሙሉ መፍታቱን ሰምተናል። በአንፃሩ የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ የፖለቲካ እስረኞችን ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት መወሰኑን ቢያበስረንም የነፃነት ታጋዩን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እስካሁን ድረስ በእሥር ቤት እየማቀቁ ነው። እዚህ ላይ አነጋጋሪው (ironic) ጉዳይ ዶ/ር አብይ የኢትዮጵያ መሪ ሆነው አገራቸው ላይ መፈፀም ያልቻሉትን የጎረቤት አገር መሪ ተማፅነው ማስፈፀም መቻላቸው ነው። ከዚህ ተነስተን ዶ/ር አብይ እንደ አንዳርጋቸው ፅጌ ያሉ አገር ወዳድ ዜጎች የበቀል ፖለቲካ ሰለባ መሆናቸው ሳያሳስባቸው ቀርቶ ነው? ወይስ እንደ ሱዳኑ መሪ የመወሰን ሥልጣን የላቸውም? የሚል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን። ሰሞኑን ከቤተ-መንግሥት አካባቢ እንደተናፈሰው ወሬ ከሆነ ዶ/ር አብይ ራሳቸው የበቀል ፖለቲካው ሰለባ ከመሆን ለትንሽ ነው የተረፉት። ስለሆነም ሀገርን መውደድና ከሥርዓቱ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንዳርጋቸው ጽጌ ልዩ የኢትዮጵያ አፈር ፦ ከጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ ~(ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ)

አንዳርጋቸው ጽጌ ልዩ የኢትዮጵያ አፈር ከጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ ~ (ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ) በ1950 ዓ.ም. ደብረብርሀን በሚገኘው የሀይለ ማርያም ማሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስገባ የዓጼ ዘርአ ያዕቆብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጽጌንና ባለቤታቸውን በየቀኑ አያቸው ነበር። ወይዘሮ አልታዬ ዘወትር በቀኝ እጃቸው እየደገፉት እሱ ድክ ድክ የሚልም ትንሽ ልጅ አይረሳኝም። የየዕለቱ ትርኢት ስለነበር . . . . ብዬ አልፌዋለሁ። ከዘመናት በኋላ እኔም አድጌና በመንግስት ስራ ኃላፊነት ቆይቼ ይህቺን አገር የሚያናውጡ ሰዎች ወደ ፖለቲካው መድረክ ሲመጡ በመጥረጊያ ከተጠረጉት የጥንት ጋዜጠኞችና የሚዲያው አመራር አባላት ጋር እዳሪ ስንጣል ያ ልጅ ይመስለኛል ከጦቢያ ቢሮ ያገኘኝ። አንዳርጋቸው ጽጌ ከመቼው በወያኔ መርከብ ተሳፍሮ ፣ ከመቼው ወርዶ፣ ከመቼው ወደ ተቃዋሚነት እንደተሸጋገረ የፖለቲካው ጉዞ ቅፅበት አልገባኝ አለ። የተቀላቀለው ቡድን አካሄድና ይልቁንም “አማራ” በተባለው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያለውን ግልጽ አቋም በመረዳት “የአማራው ህዝብ ከየት ወዴት?” የሚል መጽሀፍ ጽፎ ለህዝብ ሲያቀርብ እኔም ሆንሁ ብዕሩ እልፍ የሚጥለው ጓደኛዬ ሰውነት መልካሙ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቀን ነበር። ስለዚህ ሰውነት (በብዕር ስምነት ይቆይና) “በኢትዮጵያዊነት ላይ የተወረወረ ቦምብ” በሚል ርዕስ የራሱን ቦምብ አፈነዳ። አንዳርጋቸው አስተያየት የመስጠት መብታችንን እየጠቀሰ በመሰረቱ ግን “አቶ ሰውነት ትክክለኛው ጉዳይ የገባቸው አይመስለኝም” ብሎ ከእኔ ጋር በጦብያ ቢሮ (አክፓ ክ ነው እንባል የነበረው) ደስ የሚልና ምሁራዊ ቅባት የነበረበት ሙግት ገጠምን። ድር። በእኔ በኩል ይህን ድርጅት ፋሽስት ለማለት የፈለግሁት ኢሰብዓዊ አቋሙን ፣
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአንዳርጋቸው ዓረዓያነት ናፈቀኝ!!! (ይልቃል ጌትነት)

የአንዳርጋቸው ዓረዓያነት ናፈቀኝ!!! (ይልቃል ጌትነት) Image may contain: one or more people, people standing, outdoor and natureአንዳርጋቸውን በአካል አላውቀውም። ነገር ግን በህይወቱ የተጉዋዘውን ጠመዝማዛና ውጣ ውረድ የበዛበት መንገድ ሳስታውስ በጣም ያስደንቀኛል። ይህንን ከባድ የህይወት ጉዞ በሄደበት ጊዜ ሁሉ የሚከተለው የህይወት መመሪያ ለእኔና ከእኔ በታች ላሉ ትውልዶች ዓርዓያነቱ በጣም ከፍተኛ ነው። 1. አንዳርጋቸው በልጅነትና በጨዋታ እድሜያቸው የሀገራቸውን ፖለቲካ ለማዘመን ሲሉ የተሰዉ ለጋ ወጣት ጉዋደኞቹ ቃል ኪዳን በልቡ እንደታተመ ጨለማ ቤት እስከሚዘጋበት ድረስ ከፃፋቸውና ከተናገራቸው መገንዘብ ይቻላል። 2.አንዳርጋቸው መልካሙን በመመኘት ብቻ ለሀገራቸው ነፃነት ሲሉ በእሱ ትውልድ የነበሩ ወጣቶች የከፈሉት መስዋዕትነት ቢያስደንቀውም የሀገራቸውን ማህበራዊ ስነ ልቦናና የህብረተሰብ አደረጃጀት በውል ያልተገነዘበ መሆኑን አምኖ ባልተለመደ ሁኔታ በነፃነት ተችተዋል። 3. አንዳርጋቸው በመጀመሪያዎቹ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣባቸው ሁለት ዓመታት የሀገሩን ህዝብ የዴሞክራሲ ጥያቄ መልስ ለመስጠት በማሰብ ከኢህአዴግ ጋር አብሮ በሰራባቸው ጊዚያት ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች መንገዳቸው ሁሉ ከህዝብ ጥያቄ በእጅጉ የራቀ መሆኑን ስለተገነዘበ በራሱ ፈቃድ ድርጅቱንና ስራውን ለቁዋል። አብሮ በነበረባቸው ጊዚያት ለተሰሩ ጥፋቶች መፅሀፍ ፅፎ ህዝቡንና ሀገሩን በአደባባይ በይፋ ይቅርታ ጠይቁዋል። 4. አንዳርጋቸው የእውቀትን መሰረታዊ መርሆና ለሰው ልጅ መለወጥ አስፈላጊነትን በአፅንዖት የተረዳ ብሩህ አዕምሮ ያለው ሰው ቢሆንም ትምህርትን ለችግር መፍቻና ለማህበረሰብ አገልግሎት ለመጠቀም ብቻ ያዋለ ሲሆን ለራሱ ማህበራዊ ሽግሽግና ለግል ኑሮ ማደላደያነት የተጠቀመ ሰው አይደለም። 5. አንዳርጋቸው ሀገራችንን የወረረውን አደግዳጊነትን፣አድርባይነትን፣ አሙዋሙዋቂነትን ፣ጥራዝ ነጠቅነትን ለሀገራችን ጠንቅ መሆናቸውን ተገንዝቦ በፃፈው መፅሀፉ ውስጥ በሰፊው ያስተማረ ከመሆኑም በላይ እነዚህን ባህሪያት በመፀየፍ በተግባር
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News