የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው እስከ ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

(የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው) እስከ ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል። ይህ ለፖለቲከኞች ብቻ የማይተው የዜጎች ቀጣይ ተግባር ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በሰከነና በሰለጠነ መንገድ መልካም ጅማሮዎች ሊበረታቱ ይገባሉ፤ ነገ ሊያስከትሉ የሚችሉት ጥሩና መጥፎ ነገሮችንም በሰከነ መልኩ አትኩሮት ሰጥቶ ማሰብ ለዘላቂ ስኬት መሰረት ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያላየነውን ጭላንጭል እያየን ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከነበረው አስተዳደር ያተረፍነው ነገር ሞት እስር ስደትና መከራ ነው። ( ፖለቲካው በሴራ እስካልተያዘ ) ድረስ የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ አይወስድም ። ዶክተር አብይ አሕመድ መልካም ነገሮችን ለሕዝብ በማሳየት ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል። በቀጣይነት ደግሞ የኛ ተግባር መሆን ያለበት እየታዩ ያሉ መልካም ጅማሮዎች እንዳይከሽፉ በትግላችን ማረጋገጥ ነው።

የዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ብሔራዊ እርቅ የሚደረገውን መንገድ መጥረግም የዚህ መልካም ነገር አካል መሆኑ እያየን ነው። በጥንቃቄና በታታሪነት ሊያዝ የሚገባው የመልካም ፖለቲካ ጅማሮ ሕዝቦች በሃገራቸውና በመንግስታቸው እንዲተማመኑ በሩን ይከፍታል። የመልካም ፖለቲካ ጅማሮው እስከ ፍንጭ እስካሳየው ብሔራዊ እርቅ ሊዘልቅ ይገባል።

ፈጥኖ ከማጨብጨብ ይልቅ ፈጥኖ ማበረታታትና የተገኘው ድል እንዳይከሽፍ ከእያንዳንዱ የሰላም ሰው ጎን መቆም ያስፈልጋል። ይህ ሲባል ጎን ለጎንም መልካም ጅማሮዎችን ለማክሸፍ የሚራወጡ እኩያንን እየቀበሩ መሆን ይገባዋል። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያላየነውን ጭላንጭል እያየን ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ከነበረው አስተዳደር ያተረፍነው ነገር ሞት እስር ስደትና መከራ ነው።

አሁን ግን እነዚህ ስቃዮች በትንታግ የሕዝብ ትግሎች ፈር እየያዙ መልካምነትና ቅንነትን እየደመሩ መስመር ውስጥ ገብተዋል። እነዚህን ስኬቶች የመጠበቅ የማስቀጠል የማሳካትና ከግብ የማድረስ የእያንዳንዳችን ዜጎች ግዴታ ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ