ወደ 40 የሚጠጉ ሰብአዊ እርዳታ የያዙ የጭነት መኪኖች ወደ ትግራይ ማቅናታቸው ታውቋል።

Ethiopia

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (UNOCHA) ወደ 40 የሚጠጉ ሰብአዊ እርዳታ የያዙ የጭነት መኪኖች (ምግብን ጨምሮ) ከሰመራ ተነስተው ወደትግራይ ማቅናታቸውን አሳውቋል።

ይህ እኤአ ከጥቅምት 18 በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ያቀና የመጀመሪያው ኮንቮይ ነው።

ነዳጅ እና የህክምና ቁሳቁሶችን የያዙ የጭነት መኪናዎች ከባለስልጣናት ፈቃድ እስኪያገኙ ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

UNOCHA በትግራይ ያለው የሰብአዊነት ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ጠቁሞ፣ ወደ ክልሉ የሚደርሰው ሰብዓዊ ዕርዳታ መደበኛ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝቧል።

እኤአ ከጥቅምት 22 ጀምሮ የተቋረጠው ወደ መቐለ ከተማ የሚደረገው በረራ ከትናንትና በስቲያ መጀመሩን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ አየር አገልግሎት (UNHAS) አስታውቋል።

በአማራ ክልል ደግሞ ከ500 የሚበልጡ የጤና ተቋማት በግጭቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል በዚህም በርካታ ሰዎች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉን UNOCHA አሳውቋል።

በአፋር እና በአማራ ክልሎች ለሚቀጥሉት 2 ወራት የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናት ለማከም በቂ የስነ-ምግብ እና የመመገቢያ ቁሳቁሶች ወደ ሁለቱም ክልሎች መላካቸውን አመልክቷል።

UNOCHA የምግብ አጋሮች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በደሴና በኮምቦልቻ ከ450,000 በላይ ሰዎችን ለመርዳት የምግብ ድጋፍ ማድረግ መጀመራቸውን ሪፖርት አድርጓል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

OCHA-ETH-TigrayResponseGapAnalysis-A3-20211115 v04-11--01