ከኮሮና ምልክቶች አብዛኞቹ የሚታዩበት ቱሪስት፤ ከአ/አ አቅራቢያ በሆቴል ከተደበቀ 10 ቀን እንዳለፈው ተዘገበ

ከኮሮና ምልክቶች አብዛኞቹ የሚታዩበት ቱሪስት፤ ከአ/አ አቅራቢያ በሆቴል ከተደበቀ 10 ቀን እንዳለፈው ተዘገበ – Anteneh Yigzaw

“ወደ ውጭ ላለመውጣት ስል፣ ምግብ መኝታ ክፍሌ ድረስ እያስመጣሁ ነው የምመገበው፡፡ የግድ ከክፍሌ መውጣት ካለብኝ ግን፣ የፊት ጭንብልና ጓንት አድርጌ ነው የምወጣው… ” ብሏል፡፡
.
ከዱባይ መምጣቱና በሰሜን ተራሮችና በኦሞ ሸለቆ ለቀናት ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል

A Dubai teacher who is stranded in Africa and ill with symptoms of Covid-19 is continuing to teach his Emirates students online.Rachid El Gomri said his daily interactions with his pupils, 2,500km away in the UAE, had been his only “ray of sunshine” during an otherwise difficult time.The 46-year-old is one of thousands of residents who have found themselves stuck abroad owing to international flight restrictions following the outbreak of the coronavirus.But the Spanish teacher said he was determined to continue to support his pupils at Emirates International School in Jumeirah despite his circumstances.“My rays of sunshine have been my students,” he told The National from his hotel room in Ethiopia.

ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የመጣ እና “አብዛኞቹ የኮሮና በሽታ ምልክቶች ይታዩብኛል፤ እያመመኝ ነው” የሚል የ46 አመት ዕድሜ ያለው ፈረንሳዊ ቱሪስት፣ ከአዲስ አበባ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ መኝታ ክፍል ተከራይቶ መኖር ከመጀረ ቀናት መቆጠራቸውን ዘ ናሽናል ድረገጽ ከሰዓታት በፊት ባወጣው ዘገባ አስነብቧል፡፡
ወደ ሰሜን ተራሮች አቅንቶ እንደነበር፣ በኦሞ ሸለቆ አካባቢዎችም ለሶስት ቀናት ቆይታ እንዳረገ የተነገረለትና ራቺድ አል ጎርሚ የተባለው ይህ ግለሰብ፣ ከፍተኛ ትኩሳትና የትንፋሽ መቆራረጥን ጨምሮ አብዛኞቹ የኮሮና ምልክቶች እንደሚታዩበትና ከአዲስ አበባ የ45 ደቂቃ መንገድ ርቆ በሚገኝ አንድ ሆቴል በተከራየው መኝታ ክፍል ውስጥ መኖር ከጀመረ አስር ያህል ቀናት እንዳለፉት ለድረገጹ ተናግሯል፡፡
ግለሰቡ ጉብኝቱን ቢያጠናቅቅም የኮሮና ወረርሽኝ መስፋፋቱን ተከትሎ አለማቀፍ የጉዞ እገዳዎች በመደረጋቸው ሳቢያ ወደመጣበት ሊመለስ አለመቻሉንና አማራጭ በማጣቱ ጥሩ ሆቴል አፈላልጎ ለመከራየትና እዚሁ ለመቆየት መገደዱን የተናገረ ሲሆን፣ ስሙ ካልተጠቀሰውና ከዚህ ሆቴል መኝታ ክፍል ላለመውጣትና ከሌሎች ሰዎች ጋር ላለመገናኘት ጥረት እንደሚያደርግም ለድረገጹ በሰጠው መረጃ ገልጧል፡፡
“ወደ ውጭ ላለመውጣት ስል፣ ምግብ መኝታ ክፍሌ ድረስ እያስመጣሁ ነው የምመገበው፡፡ የግድ ከክፍሌ መውጣት ካለብኝ ግን፣ የፊት ጭንብልና ጓንት አድርጌ ነው የምወጣው፡፡ የጽዳት ሰራተኛዋንም ወደ ክፍሌ አላስገባትም፤ ሃላፊነት ይሰማኛል” ይሏል ሰውዬው፤ በአሁኑ ወቅት የሚገኝበትን ሁኔታ በተመለከተ ሲናገር፡፡
ዘ ናሽናል ድረገጽ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በዱባይ በተጣለው የጉዞ ገደብ ሳቢያ በየአገሩ ተበትነው ከቀሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች መካከል በዱባይ በሚገኝ አንድ አለማቀፍ ት/ ቤት መምህር የሆነውንና አዲስ አበባ ውስጥ ሆቴል ውስጥ የመሸገውን ይህን ግለሰብ ለዘገባ የመረጠው፣ “በሰው አገር በአንዲት ጠባብ ክፍል ታጉሮ በህመም እየተሰቃየም፣ በተስፋ አስቆራጭ የኮሮና ህመም ስሜት ውስጥ ሆኖም ከ2 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው የሚገኙ የጁሜራህ ተማሪዎቹን በኢንተርኔት አማካይነት ከማስተማር ወደኋላ ያላለ ጀግና መምህር ነው!…” በሚል አድናቆት ነው፡፡
.