በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ፣ 22 የኅብረቱ አባል አገራትና ኖርዌይ፣ ፌደራል መንግሥቱና ሕወሃት ፖለቲካዊ ንግግር እንዲጀምሩ ጠይቀዋል

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ፣ 22 የኅብረቱ አባል አገራትና ኖርዌይ፣ ፌደራል መንግሥቱና ሕወሃት ከቀጣዩ ሳምንት በፊት “ፖለቲካዊ ንግግር” እንዲጀምሩ ጠይቀዋል። አውሮፓ ኅብረት እና አገራቱ በዚህ መግለጫቸው፣ እስካሁን ተግባራዊ ባልሆኑት የግጭት ማቆም ስምምነቱ አንቀጾች አተገባበር ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጠዋል። ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ያለባቸው ዓለማቀፍ የሰብዓዊ ሕግጋትን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በሚያሟላ መልኩ እንዲሆን መግለጫው አጽንዖት ሠጥቷል። መንግሥት ተዓማኒ እና ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ እንደሚያደርጉም ኅብረቱና አገራቱ ገልጸዋል።