በ47 ቀን 12 ሾፌር 6 ተሳፋሪ በጥይት ተገድለዋል።

በ47 ቀን 12 ሾፌር 6 ተሳፋሪ በጥይት ተገድለዋል።
ከ05/01/2018 እስከ 21/02/2018 ዓም ድረስ ባለው የ46 ቀን ጊዜ በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች 12 ሾፌር እና 6 ተሳፋሪዎች ተገድለዋል። ይህ ለገፃችን የደረሰ ብቻ ነው ለእኛ ያልደረሱን ግድያዎች ይኖራሉ። ከግድያ በተጨማሪ በዚሁ ጊዜ ለቁጥር የሚታክቱ እገታዎች ተፈፅመዋል።
በሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ብዛት ያላቸው አሽከርካሪዎች ረዳቶች እና ተሳፋሪዎች በጉዞ ላይ እያሉ እየታገቱ ለፍተው ያፈሩትን ከፍለው የሚለቀቁ ነፍሳቸውን በወንበዴ ጥይት በግፍ የሚነጠቁ ሆነዋል።
አሽከርካሪዎች አፈና ግድያ እና ዝርፊያ እየተፈፀመባቸው ቢሆንም ይህንን ችግር ሚዲያዎች በዝምታ የሚመለከቱት የሰባዊ መብት ተሟጋች ነን የሚሉ በችግሩ ጥልቀት ልክ የማያወግዙት። መንግስት ችግሩን ለመፍታት በጉዳቱ ልክ ተገቢ ስራን ያልሰራበት። ብዛት ያለው ቤተሰብ ያለ አስተዳዳሪ የቀረበት ልጆች ጎዳና ለመውጣት የተዳረጉበት ጭካኔ የተሞላበት ተግባር ሁሉም ሊቃወመው ይገባል።
👉በ05/01/2018 ዓም በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ከማህደረ ማሪያም ደብረ ታቦር መንገድ ከማህደረ ማሪያም ወጣ ብሎ ህዝብ የጫነ አባዱላ ሚናባስ ሾፌር በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል።
👉በ15/01/2018 ከቀኑ ከጎንደር አዲስ ዘመን መንገድ እንፍራንዝ ወጣ ብሎ በዘራፊ ወንበዴዎች በተተኮሰ ጥይት 1 ተሳፋሪ ሕይወቱ አልፏል።
👉በ17/01/2018 ከድሬ ደዋ ጂቡቲ መንገድ ባለው የመንገድ ክፍል ከድሬ ደዋ በቅርብ ርቀት የመንገድ ክፍያ ጣቢያ አቅራቢያ የታጠቁ ወንበዴዎች 1 ሾፌር ገድለዋል
👉በ 23/01/2018 ከጎንደር መተማ ህዝብ ጭኖ እየተጓዘ የነበረ አባዱላ ሚኒባስ ላይ መቃ ወጣ ብሎ የታጠቁ ወንበዴዎች ተኩስ በመክፈት 1 ሾፌር 5 ተሳፋሪዎች ተገድለዋል።
👉በ26/01/2018 ዓም በማእከላዊ ኢትዮጽያ ክልል በጉራጌ ዞን ጊቤ በርሀ ከወልቂጤ ወረደ ብሎ ሆሌ ኬላ ዐይነስውሯ አካባቢ 1 ሾፌር በወንበዴዎች ተገድለል።
👉በ29/01/2018 ከባቲ ወጣ ብሎ በታጠቁ ወንበዴዎች 1 የአምቡላንስ ሾፌር ተገድሏል።
👉በ07/02/2018 በመትሀራ እና አዋሽ መሀከል አካባቢ ብሬከሩ ላይ ይታጠቁ ወንበዴዎች አንድ ረዳትን በጥይት በመግደል መኪና አቃጥለዋል።
👉በ 08/02/2018 በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ጉትን መንደር 10 አካባቢ የታጠቁ ወንበዴዎች 1 ሾፌር በጥይት ተገድሏ።
👉በ 11/02/2018 ወልቂጤ መግቢያ ሆሌ ኬላ አለፍ ብሎ በታጠቁ ወንበዴዎች ነፍስ አጥፊዎች 1 ሾፌር በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል
👉በ18/02/2018 ዓም በሰከላ እና በቲሊሊ መሀል በምትገኝ አምብሲ ተብላ በምትጠራ ትንሽ መንደር አቅራቢያ 1 ሾፌርተገድሏል
👉20/02/2018 በአማራ ክልል ከወረታ ደብረ ታቦር መንገድ ወጂ አካባቢ 1 ሾፌር ተገድሏል
👉21/02/2018 በአማራ ክልል ብርቁ የሚባል ሾፌር ከአዲስ ዘመን እንፍራንስ መሀል ሰብሀ ላይ ተገድሏል።
በምስሉ የሚታዩት በዘራፊ ወንበዴዎች በግፍ በጥይት ከተገደሉት ውስጥ ያሉ ናቸው ነፍስ ይማር
የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲህ ያሉ የግፍ ግድያዎችን በጉዳቱ ስፋት ልክ የማይዘግቡበት ድምፅ ሆነው ችግሩን ለማሳየት የማይጥሩበት ሁኔታ የሚያሳዝን የሚያሳፍት ከሰባዊነት ቦታ የራቁ ለዜጎች ሞት የማይጨነቁ ከሙያው ስነ ምግባር የራቁ መሆናቸውን ያየንበት ነው።
መንግስት በችግሩ ጥልቀት ልክ ሊሰራ ይገባል ችግር በሚፈፀምባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ድርጊቶችን ሊያዎግዙ ዘራፊ ነፍስ ቀጣፊ የሆኑ ግለሰቦችን ሊቃወሙ ይገባል።
ፍትህ በግፍ ለሚገደሉ።