” ታዳጊዎቹ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው ሞተው የተገኙት። ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው ” – በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ተወካይ
ነዋሪነታቸዉን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ያደረጉ ዲቦራ መንግስቴ እና ኦፕራ መንግስቴ የተባሉ ሁለት እህታማማቾች በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ተወካይ ኮሚቴዎች መካከል አቶ ዓለማየሁ ቲጁማ አሳውቀዋል።
በሁለቱ እህትማማቾች አሟሟት ዙሪያ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ያነሱት አቶ ዓለማየሁ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ” በካምፓስ /ዩኒቨርሲቲ/ውስጥ ሞተው ተገኙ ” በሚል የተሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱና ከእውነታዉ የራቁ ናቸው ብለዋል።
አስክሬናቸው በደቡብ አፍሪካ ሕዝባዊ ሽኝት ተደርጎ ነገ ዐርብ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላክም ገልፀዋል።
