በትግራይ ላይ ላለፉት አምስት ዓመታት የቀጠለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሁለት ወር ነው ብሎ አብይ አሕመድ አቅልሎታል

ሕወሃት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላይ ባደረጉት ንግግር የትግራዩ ጦርነት የሁለት ወራት ጦርነት ነበር በማለት፣ በትግራይ ላይ ላለፉት አምስት ዓመታት የቀጠለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ አቅልለው ለማቅረብ ሞክረዋል በማለት ከሷል። ሕወሃት፣ የዐቢይ ንግግር በትግራይ ሕዝብ ሞት እና ስቃይ ምን ያህል እያፌዙ እንደሆነ እና ለቀድሞ ጥፋታቸው ንስሃ እንደማይገቡ ያሳያል በማለት ተችቷል። የግጭት ማቆም ስምምነቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አሁን አደጋ ላይ መውደቁን ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ማወቅ አለበት ያለው ሕወሃት፣ የአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪ አካል ኹኔታውን ለመገምገም አስቸኳይ ስብሰባ እንዲቀመጥ ጠይቋል።