Blog Archives

መደማመጥና መነጋገር ከቻልን የማንፈታቸው ልዩነቶች የሉም!!!

አገራችን እና ሕዝቧ በአንድ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መዳፍ ውስጥ ናቸው። በአገራችን የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የግለሰብም ሆነ የቡድን መብቶቻቸው ተረግጠው በባርነት እየተገዙ፤ ጉልበታቸውና ሃብታቸው እየተመዘበረ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምገኝ ዜጎችና ማኅበረሰቦች ሁሉ እጣ ፈንታችን ተሳስሯል። ሁላችንም ነፃ ካልወጣን በስተቀር ማናችንም በተናጠል …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ጠላት ጆሮው እየሰማ ዓይኑም እያየ ለክብራችን በአንድነት ጸንተን እንቆማለን!!!

ህወሃት ልዩነቶቻችንን አብዝቶና አርብቶ ክብራችንን አዋርዶ ረግጦ ሊገዛን ዘመኑን ሙሉ ሠርቷል። ለብዙ ግዜም አንዱን ህዝብ የአንዱ ጠላት አድርጎ ሲሰብክ ኑሯል። ይህንንም እውነት ለማስመሰል በበደኖ ፤በአርባ ጉጉ፤ በሃረርጌና በሌሎች ሥፍራዎች የብዙ ንጹሃን ዜጎችን ደም አፍስሶ ለርካሽ ፖለቲካ ፍጆታ አውሎታል። በደኖ ላይ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በምእራብ ጎጃም ሁለት የወያኔ ሹሞች ሲገደሉ ሁለት ፖሊሶችና አንድ ሌላ ጄሌ መቁሰላቸው ተዘገበ

በአማራ ክልል ሥር በሚገኘው የምዕራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ ሁለት የወያኔ ሹሞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ ጄሌ ባለስልጣን ከፉኛ መቁሰላቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ዜና ገለጸ።

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ባለፈው ረቡዕ ጥር …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በምእራብ ጎጃም ሁለት የወያኔ ሹሞች ተገደሉ

በአማራ ክልል ሥር በሚገኘው የምዕራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ ሁለት የወያኔ ሹሞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ ጄሌ ባለስልጣን ከፉኛ መቁሰላቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ዜና ገለጸ።

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ባለፈው ረቡዕ ጥር …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች የሚያደርጉትን አድማ እንደቀጠሉ ነው። በነቄምት ዩኒቨርሲት 2 ተማሪዎች መገደላቸው ተዘገበ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት እንደዘገበው ከሳምንት በፊት የተጀመረው የአወሊያ ኮሌጅ ተማሪዎች ተቃውሞ እየከረረ በመሄዱ የወያኔ የጸጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተው የኮሌጁን ግቢ ዘግተው ተቀምጠዋል።

መንግሥት ተብዬው አገዛዝ ያሰማራቸው የኮሌጁ ባለሥልጣናት አለአግባብ የትምህርት ይዘቱን በመቀየራቸውና መምህራንን በማባረራቸው የተቆጡት …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ሃሰትን እንድናገር ያስገደደኝ መንግስት ነው ማለት አያዋጣም!!!

በዘረኛው ቡድን አማካኝነት የአገራችን የሞራል እሴቶች ሆን ተብለው እየተዋረዱ ነው።ድሮ ድሮ “እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር” የሚባል መልካም አባባል ነበረን። ዛሬ ይህን የመሰሉ አባባሎች ከል እንዲለብሱ በመደረጉ እውነትን  የሚናገር በግዞት ተይዞ የመከራ እንጀራ ይበላል የመከራ ውሃም ይጠጣል።

እንደ ንጉስ አክዓብ በዙሪያው …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በጀኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የወሰደውን አቋም በመደገፍ ግንቦት7ና ጥምረት መግለጫ አወጡ

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥላ ሥር ከሌሎች የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑን ገሃድ ማድረጉን ተከትሎ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከትናንትና በስቲያ መግለጫ አውጥቶአል።

“የጋራ ትግል የጋራ አገር” በሚል ርዕስ ግንቦት7 …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ደንበኞቻቸው ከ200 ሺ ወይም ከ10 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የመረጃ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዙ

የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በፍርሃት ለማሸምቀቅ ተብሎ በዘረኛው መለስ ዜናዊ የተቋቋመው የጸረ ሽብር የመረጃ መእከል የተባለው መሥሪያቤት ለግልና ለመንግስት ባንኮች ባወረደው መመሪያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ የውጭ አገር ዜጋ ከ200 ሺ ብር ጀምሮ በባንኮች ለማስቀመጥ ወይም ለማውጣት በሚሄድበት ጊዜ፣ ባንኮች የግለሰቦችን ስምና ማንነት …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

የቀድሞ ህወሃት መስራች የነበሩና በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመድረክ ፓርቲ አባል የሆነው የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ ከመንገድ ላይ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ

አቶ አስገደ ከፍርድ ቤት ሆነው በስልክ ለፍትህ ጋዜጣ እንደገለፁት ከሆነ፣ ከሳሻቸው የቀድሞው የሕወሓት አባል የሆነው ብስራት አማረ ሲሆኑ ጉዳዩን የያዘቺው ዳኛ ደግሞ የቀድሞዋ የህወሓት ታጋይ ኪዳን አብርሃ ናት ተብሎአል።

ክስ የቀረበባቸውም ከዚህ ቀደም በፃፉት “ጋሀዲ” በተሰኘው መፀሀፍ እንደሆነ አቶ አስገደ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ወያኔ በሙስሊም ሃይማኖት ውስጥ እያደረገ ካለው ጣልቃ ገብነት አለመታቀቡ ምዕመናኑን ማስቆጣቱን ቀጥሎአል

ህዝብን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ መግዛት ብቸኛ የህይወት እስትንፋሱ የሆነው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፤ ቀደም ሲል በአገራችን ሙስሉም ህብረተሰብ ዘንድ ፈጽሞ የማይታወቅ አህባሽ የተባለ የእምነት ትምህርት በሃይል ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ዘመቻ በተለያየ የአገራችን ክፍል የሚኖሩ ሙስሊም ወገኖቻችን እየተቃወሙት መሆኑ እየተዘገበ ነው።

በመለስ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በስዊድናዊያኑ ላይ የተላለፈውን የግፍ ብይንና የቅጣት ውሳኔን እንቃወማለን፤ የኢትዮጵያዊያኑ ጉዳይ ደግሞ ያስጨንቀናል!!!

የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ችሎት በስዊድናዊያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብየ እና ጆአን ፐርሰን ላይ የጥፋተኝነት ብይን ከሰጠ በኋላ እያንዳንዳንዳቸውን በአስራ አንድ ዓመታት ጽኑ እስራት መቅጣቱ መላውን ዓለም አስቆጥቷል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄም እነዚህን የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ችሎት ውሳኔዎችን አጥብቆ ያወግዛል።…

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

መለስ ዜናዊ ከማንም አይሻልም!!!

መለስ ዜናዊ ከደርጉና ከአጼዎቹ ጋር ራሱን እያወዳደረ እኔ እሻላችኋለው እያለ ሲሰብክ እነሆ ሦስት አስርተ ዓመታትን አስቆጥሯል። ይሄንንም ስብከት ያመኑ ብዙ ሰዎች መኖራቸውም እውነት ነው።

መለስ ዜናዊ  ዘመኑ ከደረሰበት የእደገት ደረጃ  እጅግ ወደ ኋላ እርቆ የሚጓዝ ክፍ ዘረኛ በመሆኑ ሁል ግዜ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ታማኝነታቸው እየመነመነ የመጣ ባለ ከፍተኛ ማዕረግ የጦር አባላትን በጡረታ አባረረ። አብዛኞቹ ተባራሪዎች የሌሎች ብሔረሰብ አባላት መሆናቸው ታወቀ

የወያኔ መከላከያ ሚንስቴር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ዜና በወያኔ የመተካካት ፖሊሲ በመከላኪያ ሠራዊት ውስጥ ካሉት ከፍተኛ ባለማዕረጎች ውስጥ 13 ጀኔራሎችና 303 ሌፍቴናንት ኮሌነልነትና ሙሉ ኮሌነል ማዕረግ ያላቸው አባላት በጡረታ ስም ከሰራዊቱ መገለላቸው ታውቆአል።

የግንቦት7 ምንጮች መረጃ እንደሚያመለክተው ግን በጡረታ ከተገለሉት አብዛኞቹ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በዳርፉር አመጽያን መሪ ግድያ ዙሪያ የወያኔ እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር ተዘገበ። መለስ ዜናዊ የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን የማስገደል ዕቅድ እንዳለው ተጋለጠ

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ኢሳት በትናትና ዜናው እንደዘገበው፤ የዳርፉር አማጺ መሪ የነበሩት ዶ/ር ካሊል ኢብራሂም ግዲያ ላይ የወያኔ እጅ ያለበት መሆኑን የሚያመለክት ፍንጮች መገኘታቸውና የዘረኛው መለስ ዜናዊ አፈቀላጤ የሆነው በረከት ስሞኦን ከግዲያው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ካርቱም ውስጥ ከሱዳን ከፍተኛ የደህንነት …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

የወያኔ ፍርድ ቤት በስዊድን ጋዜጠኞች ላይ ያስተላለፈው ቅጣት አለም አቀፍ ተቃውሞ ቀስቅሶአል

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ ለመታዘብ ወደ ክልሉ ሲገቡ የተያዙትና በወያኔ ፍርድቤት የአስራ አንድ አመት ጽኑ እስራት የተፈረደባቸው ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ጉዳይ ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፍ ተቃውሞ በአገዛዙ ላይ ማስነሳቱን የዝግጅት ክፍላችን አረጋገጠ።

የወያኔ ፍርድ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ደቡብ ክልል በወያኔ ግምገማ እየተተራመሰ ነው ተባለ ። አርበኛው የኔሰው ገብሬ የከፈለውን ህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ለማሳጣት የስም ማጥፋት ዘመቻ ያካሄደው ባለሥልጣን ከሃላፊነቱ ተባረረ። ሃያ ሰባት የመኢአድ አባላት በደቡብ ክልል በወያኔ ካድሬዎች ታሰሩ

በህወሃት የሚመራው ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በተለያየ ሹመትና ጥቅማ ጥቅሞች የራሱ ምርኮኛ አድርጎ የሚገለገልባቸውን የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች በአዳዲስ ታዛዦች ለመተካት ዘወትር በሚጠቀምበት ግምገማ ሰሞኑን በደቡብ ክልል በርካታ ሰዎች ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ መባረራቸውን የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ኢሳት በትናንትና የዜና ዘገባው አስታወቀ።…

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ንብረት አውድመዋል የተባሉ 52 ተማሪዎች መቀጣታቸውን ተገለጸ

በማንኛውም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ወጣት ዜጎች በአገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ወያኔን በሚቃውም መልኩ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳያደርጉ ለማገድ ለሥርዓቱ ታማኝ የሆነ አስተዳደር በየትምህርት ቤቶቹ ከማቋቋም ጀምሮ ለነጻነታቸውና ለመብታቸው የሚቆረቆሩትን አድኖ ከትምህር ገበታቸው በማባረር ተግባር ላይ የተሰማራው የመለስ ዜናዊ ዘረኛ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ “በለሎች እስረኞች ላይ በሃሰት መስክሪና በነጻ ትለቀቂያለሽ ተብዬ በሃሰን ሺፋና ሌሎች ወንጀል መርማሪዎች ተጠይቄ እምቢ በማለቴ ጨለማ ውስጥ ለ13 ቀናት ታግቼያለሁ” ስትል ለወያኔ ፍርድ ቤት ችሎት ተናገረች

ወጣቷ ሴት ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ይህንን የወያኔ ከፍተኛ ወንጀል መርማሪዎች ተንኮል ያጋለጠቺው ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የወያኔ ፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ፊት ቀርባ የተመሰረተባትን የሽብርተኝነት ክስ እንድታስተባብል በተጠየቀችበት ወቅት እንደሆነ ዘጋቢያችን ከስፍራው ከላከልን ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል።…

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ግንቦት 7 የወያኔ ፍርድ ቤት በሁለቱ የሲውዲን ጋዜጠኞች ላይ ያስተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በማውገዝ በአስቸኳይ እንዲፈቱ የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ

ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ያወገዘውና አለም አቀፍ ህብረተሰብ የሚችለውን ሁሉ ጫና አድርጎ ያለምንም ቅድሜ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቀው ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 15 ቀን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባወጣው መግለጫ ነው።

“ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ዝርፊያም ዘረኝነትም፤ በቃን !!!!

የኢትዮጵያን ፓለቲካና ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው የድሆችን ደም እየመጡ ያሉት የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ሎሌዎች እአአ ከ1990 መጀመሪያ እስከ 2007 መጨረሻ በነበሩት 18 ዓመታት ውስጥ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ ማሸሻቸው የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃግብር (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) በጥናት ማረጋገጡን ይፋ ካደረገ አንድ ዓመት …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ሃሰተኛ – ብርቱ ወንጀለኛ!!!

ከግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ ታህሳስ 8  2004

ሰለ ሃሰት – በተለይም በሃሰት ስለመመስክር – አባቶቻችንና እናቶቻችን ያቆዩልን በርካታ ሥነ-ቃሎች አሉን። አንዱ በአርዕስትነት የተጠቀምንበት “ሃሰተኛ፤ ብርቱ ወንጀለኛ!” የሚለው ነው።

ለራሳቸው፣ ለአገራቸውና ለወገናቸው ነፃነት ሲሉ የተቃውሞ ድምጽ ባሰሙ ወገኖቻችን ላይ የመለስ ዜናዊ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

ህወሃትን መደገፍ በምንም መንገድ አማራጭ አይሆንም!!!

አንዳንድ ሰዎች ህወሃትን የምንደግፈው አማራጭ ስላጣን ነው ሲሉ ይደመጣሉ። እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ የሚመጣው ነገሮችን ከሥር መሰረቱ ለማየት አቅም ከማጣት ብቻ ሳይሆን የራስን ችሎታና እውቀት ፈልጎ ካለማግኝትም ጭምር የሚፈጠር እምነት ነው።

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የተባለው ዘረኛና ዘራፊ ድርጅት ኢትዮጵያዊያንን አማራጭ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

የሠራዊቱን የብሔር ተዋጽኦ ለማመጣጠን የምልመላ መስፈርቶች ዝቅ እንዲል ተደርጎአል ሲል የወያኔው የመከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ

በህወሃት የበላይነት በሚመራው የአገሪቱ መከላኪያ ሠራዊት ውስጥ ያለው የአዛዥነት ቦታ ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከትግራይ ብሄር በመጡ ጎጠኞች መያዙን የግንቦት 7 ንቅናቄ ካጋለጠ ወዲህ፤ የብሄረሰብ ተዋጾ ለማመጣጠን በሚል የተለያዩ የማስመሰያ ጥገናዊ ለውጦች ሲነገሩ የቆዩ ቢሆንም ሲራጅ ፋጌሳ በተባለው የይስሙላ …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

የህወሀት ጄኔራሎችና ኩባንያቸው ኢፈርት በጦር መሳሪያ ሺያጭ ውስጥ እንደተዘፈቁና በጎሬቤት አገር ዘረፋ እያካሄዱ መሆኑ ተዘገበ

ድርጅታቸው ህወሃትን ለድል በማብቃታቸው ለጄኔራልነት ማዕረግ የበቁት የቀድሞ “የትግራይ ታጋዮችና” የንግድ ድርጅታቸው ኢፈርት በአገር ውስጥ የሚያካሂዱትን ዘረፋ አድማስ በማስፋት ከሁለት አስርተ አመታት በላይ በጦርነት እየተታመሰች ካለቺው ጎሬቤት አገር ሱማሊያ ተገንጥላ ካለቺው ፑትላንድና ከአዲስቷ የደቡብ ሱዳን ተለይታ የራሷን አስተዳደር ለመመስረት ትግል …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic

የወያኔ ፍርድ ቤት በሰላም ታጋዮችና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተፈበረከውን የፈጠራ ወነጀል ክስ አስመልክቶ የቀረቡትን የሃሰት ምስክሮች ቃል ሰምቶ እንደጨረሰ ተገለጸ

በዘረኛው መለስ ዜናዊ ቃል የሚመዘወረው የወያኔ ፍርድ ቤት በነ አንዱአለም አራጌና ሌሎች 24 ሰዎች ላይ የተፈበረከውን የፈጠራ ክስ በማስረጃ ለማጠናከር በውሸት እንዲመሰክሩ ስልጠና ወስደው የቀረቡትን 30 ሰዎች ምስክርነት ቃል አድምጦ ሌላ ተጨማሪ የኦዲዮና የቪዲዮ ማስረጃ ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠ የደረሰን …

Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic