ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ “በለሎች እስረኞች ላይ በሃሰት መስክሪና በነጻ ትለቀቂያለሽ ተብዬ በሃሰን ሺፋና ሌሎች ወንጀል መርማሪዎች ተጠይቄ እምቢ በማለቴ ጨለማ ውስጥ ለ13 ቀናት ታግቼያለሁ” ስትል ለወያኔ ፍርድ ቤት ችሎት ተናገረች
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወጣቷ ሴት ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ይህንን የወያኔ ከፍተኛ ወንጀል መርማሪዎች ተንኮል ያጋለጠቺው ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የወያኔ ፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዴታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ፊት ቀርባ የተመሰረተባትን የሽብርተኝነት ክስ እንድታስተባብል በተጠየቀችበት ወቅት እንደሆነ ዘጋቢያችን ከስፍራው ከላከልን ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል።…