ደቡብ ክልል በወያኔ ግምገማ እየተተራመሰ ነው ተባለ ። አርበኛው የኔሰው ገብሬ የከፈለውን ህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ለማሳጣት የስም ማጥፋት ዘመቻ ያካሄደው ባለሥልጣን ከሃላፊነቱ ተባረረ። ሃያ ሰባት የመኢአድ አባላት በደቡብ ክልል በወያኔ ካድሬዎች ታሰሩ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በህወሃት የሚመራው ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በተለያየ ሹመትና ጥቅማ ጥቅሞች የራሱ ምርኮኛ አድርጎ የሚገለገልባቸውን የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች በአዳዲስ ታዛዦች ለመተካት ዘወትር በሚጠቀምበት ግምገማ ሰሞኑን በደቡብ ክልል በርካታ ሰዎች ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ መባረራቸውን የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ኢሳት በትናንትና የዜና ዘገባው አስታወቀ።…