Blog Archives

መሳጭ የሐዋሳ ትዝብት (በታሪኩ ወዳጆ)

*መሳጭ የሐዋሳ ትዝብት (በታሪኩ ወዳጆ) ፨ ናፍቄ ከምጎበኛት ሐዋሳ በምጥና በጭንቀት ወጣሁ፡፡ ፨ ለሁለት ተከፍለው ድምጻቸወን ለዶ.ር. አብይና ለሽፈራው ሽጉጤ የሰጡ ኹለቱ ወገኖች ነገር ፨የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደሴ ዳልኬ፣ የለውጥ ኃይሉን የሚደግፉ ሆነው ሳለ ስለቀውሱ የሚሰጡት መግለጫ ግን የተቃራኒው ነወ፡፡ ፨ፖሊሶች ችግር ባለባቸው ቦታዎች ደርሰው እንኳን ችግሩን ተቆጣጥረው ማረጋጋት ሲጀምሩ ባስቸኳይ ውጡ የሚል መመሪያ እየደረሳቸው ሲበሳጩ አይቻለው፡፡ ፨አብዛኛዎቹ አፈናቃዮችና ተፈናቃዮች በአንድ ቤተ እምነት አብረው የሚያመልኩ፣ጎን ለጎን ሆነውአብረው የዘመሩ ናቸወ፡ ፨የሐሰት ወሬ ከሚነዙት መካከል የክልሉ ልዩ ኃይሎች ጭምር ይገኙበታል፡፡ የተፈጠረው ግርግር ቀለል ያለ ነው በሚል እምነት ረቡዕ ማታ (ሰኔ 6 ቀን 2010) ሐዋሳ ከተማ ለስራ ገባሁ፡፡ ስደርስ ከተማዋ ጭር ብላለች፡፡ እየገረመን ሻንጣችንን ሴንትራል ሆቴል አስቀምጠን እራት ፍለጋ ወጣን፡፡ ያ ሁሉ የሐዋሳ ምግብ ቤት ዝግ ነው፡፡ ከኛና ፓትሮል ከሚያደርጉ መኪኖች በቀር መንገድ ላይ ሌላ አይታይም፡፡ ወደ ሆቴላችን ተመልሰን እዚያው የተገኘውን ተቃምሰን አደርን፡፡ ሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል አካባቢ በሐዋሳ ከተማ የተሰማሩ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የአጋዚ ወታደሮች፣ የተሰማሩበት ስፍራ ነው፡፡ ሐሙስ ጠዋት ቀጠሮ ወደያዝኩበት መስሪያ ቤት አምርቼ ሰርቼ፣ ምሳ ሰዓት ላይ አንዳንድ ግጭቶች ስለተስተዋሉ፣ ማየት የምፈልገውን ዶክመንት ይዤ ወደ ሆቴል አመራሁ፡፡ ስለራሴ ሆነ ስለከተማዋ ደህንነት መረጃ ለመቃረም እየሞከርኩ እኒህን ሁኔታዎች በአይኔ ተመለከትኩ፣ በጆሮዬም ሰማሁ፡፡ 1. ደህዴን ተከፍሏል፡፡ የለውጥ ኃይሉን የሚደግፉና የሚቃወሙ የደህዴን አባላት በሁለት ጎራ ተከፍለው እየተፋለሙ ነው፡፡ ይህ ልዩነት ዶ.ር. አብይ ወደ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሲዳማ ዞን ለኩ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ናት ። (ቪድዮ)

በሲዳማ ዞን ለኩ ከተማ ገበያ ዳር የሚገኙ ሱቆች ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል እንዲሁም የወፍጮ ቤቶችና የመኖሪያ ቤቶች ጋይተዋል።  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News