Blog Archives

እውነቱ ክፉ አረመኔ መሆናችን ነው ! (መስከረም አበራ)

እውነቱ ክፉ አረመኔ መሆናችን ነው ! (መስከረም አበራ) “የእንትን ህዝብ ሰው አክባሪ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ እንስፍስፍ ነው” የሚለው የአልኩ ባይ፣ አለባባሽ፣አስመሳይ ፣እና ግብዝ ፖለቲከኞች እና ዘረኛ አክቲቪስቶች ዲስኩር እኛን አይገልፀንም፨ እኛን የሚገልፀን እርኩስ አረመኔነትን ሰንቀን የምንዞር ሰው መሳዮች መሆናችን ነው ! ፖለቲከኞቹ ሃቅን በማለባበስ ነገር ያሳመሩ ስለሚመስላቸው ነው፨ ዘረኛ አክቲቪስቶች ለብሄረሰባቸው የመለዓክት ክንፍ ለመትከል የሚሞክራቸው ያው የዘረኝነቱ አካል ሲሆን ከተራ ዘረኝነት የዘለለ አረመኔያዊ ተግባር በሰፈራቸው ሰዎች መፈፀሙ የማይናገሩት ግን የሚጋሩት ርጋፊ አረመኔያዊ ስሜት ስላላቸው ነው፨ በአይን የሚታየውን ሃቅ አለባብሶ እና አቅልሎ መናገር በጉዳዩ የማዘን ወይ የመከፋት አለያም ከጥፋት መፀፀት የመፈለግ ምልክት አይደለም፨ ይልቅስ ዘሮቻቸው የፈፀሙት እርኩሰት ጀብዱ እየመሰላቸውም ይሆናል፨ በበኩሌ አንድ ፍሬ ልጅ ኡኡ እያለ ከመሬት ጋር እስኪመሳሰል ሲቀጠቀጥ እያየሁ የእንትን ህዝብ እንስፍስፍ ነው ቢሉኝ ስሜታዊ ያደርገኝ ይሆናል እንጅ ትርጉሙ አይገባኝም! የሃዋሳ ነዋሪ እንደመሆኔ የሆነውን ነገር ሁሉ በአይኔ አይቻለሁ፨ ምን እንዳጠፋን ሳናውቅ ሞት ሆ ብሎ በደጃችን አልፏል፨ የእኛን ቤት ለዛሬ ያለፉት ቡድኖች እኛን ስላልነኩን ነገ ዋስትና አለን ማለት አይደለም፨ ከሁሉም በላይ በወላይታ ወንድም እህቶቻችን ላይ ያደረጉት አላመመንም ፣ልባችንን አልሰበረውም ማለት አይደለም፨ ወላይታ ስራ ያለበት ሁሉ ሃገሩ ነው፨ እንጀራ ፍለጋ በገፍ በሃገሪቱ ዳርቻ መበተኑ የጎሳፌደራሊዝሙ ተጠቂ አድርጎታል፨ በሃዋሳ የሆነባቸው ሁሉ ልቤን ሰብሮታል ፤ ሰው ልጠላ ሞክሮኛል፨ የዛሬው አንድ ፍሬ ልጅ ከመቅፅበት አፈር ትቢያ ሲሆን ያየሁት ቪዲዮ ስሜቴን ረብሾታል ፣”ለምን እዚህ ሃገር ተፈጠርክ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ ።

Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለውይይት ወደሃዋሳና ሶዶ አመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑ በሀዋሳ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡ከ8 መቶ በላይ ነዋሪዎችም እየተሳተፉ ነው፡፡የአገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል መንግስትና የክልል ኃላፊዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ውይይቱን ኢቲቪ እንደሚከተለው ዘግቦታል… በፊቼ ጫምባላላ ላይ ግጭት እንዲፈጠር ያደረጉትን መንግስት ለሕግ ያቀርባቸዋል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በፊቼ ጫምባላላ ላይ ለተፈጠረው ግጭትና የደረሰው ጉዳት እንዲሁም የሲዳማ ህዝብ “የክልል እንሁን” ጥያቄዎችን ሲመልሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንደገለጹት፣ በፊቼ ጫምባላላ ጊዜ ለሰው ደም መፍሰስ ምክንያት የሆኑ ግለሰቦችን መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለሕግ ያቀርባቸዋል፡፡ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ለማንሳት ሕገ መንግስቱ ይፈቅድለታል፤ ነገር ግን ጥያቄው በሕገ መንግስታዊ መንገድ ነው የሚፈታው፣ እናንተም ለምን ክልል መሆን አስፈለገን ብላችሁ ከታች እስከ ላይ በሚገባ ተወያዩ እኛም እንወያያለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዋሳ ከተለያዩ የማህበረሰብ አካላት ጋር ውይይት ካደረጉና ከማህበረሰቡ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ከሰጡ በኋላ ከሰዓት በወላይታ ሶዶ ተመሳሳይ ውይይት ለማድረግ ወደ ስፍራው ተጉዘዋል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መሳጭ የሐዋሳ ትዝብት (በታሪኩ ወዳጆ)

*መሳጭ የሐዋሳ ትዝብት (በታሪኩ ወዳጆ) ፨ ናፍቄ ከምጎበኛት ሐዋሳ በምጥና በጭንቀት ወጣሁ፡፡ ፨ ለሁለት ተከፍለው ድምጻቸወን ለዶ.ር. አብይና ለሽፈራው ሽጉጤ የሰጡ ኹለቱ ወገኖች ነገር ፨የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደሴ ዳልኬ፣ የለውጥ ኃይሉን የሚደግፉ ሆነው ሳለ ስለቀውሱ የሚሰጡት መግለጫ ግን የተቃራኒው ነወ፡፡ ፨ፖሊሶች ችግር ባለባቸው ቦታዎች ደርሰው እንኳን ችግሩን ተቆጣጥረው ማረጋጋት ሲጀምሩ ባስቸኳይ ውጡ የሚል መመሪያ እየደረሳቸው ሲበሳጩ አይቻለው፡፡ ፨አብዛኛዎቹ አፈናቃዮችና ተፈናቃዮች በአንድ ቤተ እምነት አብረው የሚያመልኩ፣ጎን ለጎን ሆነውአብረው የዘመሩ ናቸወ፡ ፨የሐሰት ወሬ ከሚነዙት መካከል የክልሉ ልዩ ኃይሎች ጭምር ይገኙበታል፡፡ የተፈጠረው ግርግር ቀለል ያለ ነው በሚል እምነት ረቡዕ ማታ (ሰኔ 6 ቀን 2010) ሐዋሳ ከተማ ለስራ ገባሁ፡፡ ስደርስ ከተማዋ ጭር ብላለች፡፡ እየገረመን ሻንጣችንን ሴንትራል ሆቴል አስቀምጠን እራት ፍለጋ ወጣን፡፡ ያ ሁሉ የሐዋሳ ምግብ ቤት ዝግ ነው፡፡ ከኛና ፓትሮል ከሚያደርጉ መኪኖች በቀር መንገድ ላይ ሌላ አይታይም፡፡ ወደ ሆቴላችን ተመልሰን እዚያው የተገኘውን ተቃምሰን አደርን፡፡ ሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል አካባቢ በሐዋሳ ከተማ የተሰማሩ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የአጋዚ ወታደሮች፣ የተሰማሩበት ስፍራ ነው፡፡ ሐሙስ ጠዋት ቀጠሮ ወደያዝኩበት መስሪያ ቤት አምርቼ ሰርቼ፣ ምሳ ሰዓት ላይ አንዳንድ ግጭቶች ስለተስተዋሉ፣ ማየት የምፈልገውን ዶክመንት ይዤ ወደ ሆቴል አመራሁ፡፡ ስለራሴ ሆነ ስለከተማዋ ደህንነት መረጃ ለመቃረም እየሞከርኩ እኒህን ሁኔታዎች በአይኔ ተመለከትኩ፣ በጆሮዬም ሰማሁ፡፡ 1. ደህዴን ተከፍሏል፡፡ የለውጥ ኃይሉን የሚደግፉና የሚቃወሙ የደህዴን አባላት በሁለት ጎራ ተከፍለው እየተፋለሙ ነው፡፡ ይህ ልዩነት ዶ.ር. አብይ ወደ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሐዋሳ ከተማ በሲዳማና ወላይታ ብሔር ተወላጆች መካከል የከረረ ግጭት ተፈጥሯል፡፡

በሐዋሳ ከተማ በዋናነት በሲዳማና ወላይታ ብሔር ተወላጆች መካከል የከረረ ግጭት ተፈጥሯል፡፡ የንግድ ቤቶች በግድ እንዲዘጉ እየተደረጉ ሲሆን በወላይታና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ድብደባና ወከባ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ በቦታው ወደሚገኝ ግለሰብ ጋር ስልክ ደውዬ እንዳረጋገጥኩት በተለይ አሮጌ ገበያ በሚባለው አከባቢ ነዋሪዎች መስራትም ሆነ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በመሆኑም ነገሮች ከቁጥጥር ከመውጣታቸው በፊት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአስቸኳይ ምላሽ ሊሰጡ ይገባል፡፡ በተያያዘ ዜና በወልቅጤ ከተማ በሚኖሩ የጉራጌ ብሔር ተወላጆችና በከተማዋ ዙሪያ ባሉት የቀቤና ማህብረሰብ ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአሁን ሰዓት ከወልቂጤ ወደ ወሊሶ የሚደረገው የህዝብ ትራንስፖርት ተቋርጧል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News