• አለዚያ፣ ህግና ስርዓት፣ ለጉልበት ወይ ለትርምስ ተሸንፎ ማጣፊያው ያጥረናል።
• “የሕዝቡ ጥያቄ ስላልተደመጠ ነው” ብሎ ያሳብባል አንዱ ምሁር። (ጥፋትና ጭካኔን የሚያስውብተዓምረኛ እውቀት የያዘይመስል።)
• “መንግስት ፈጣን ምላሽ ስላልሰጠ ነው” ይላል አንደኛው ፀሐፊ ። (ክፋትንና ምቀኝነትን የሚያቆነጅ ልዩ አስማት ያገኘ ይመስል።)
• “የመወያየትና የመነጋገር እድል ስለሌለ ነው” ይላል አንደኛው ፖለቲከኛ (በዚህች ንግግሩ፣ ወንጀልን እንደፍትህ የሚቆጠርለት ይመስል።)
በአሉባልታ ጭፍን ጥላቻንና ዛቻን የሚዘሩ፣… የሰውን ንብረት የሚዘርፉና የሚያቃጥሉ፣… ሰውን ከመኖሪያው የሚያሳድዱና የሚገድሉ ወንጀለኞችን ለማቆንጀት፣ እንደበቀቀን ነጋ ጠባ፣ ማሳበቢያ ቃላትን ማነብነብ፣ ማመካኛ አባባሎችን ሌት ተቀን መደጋገም ይብቃ!
የስንቱ ሕይወት ጠፋ? የስንቱ አካል ጎደለ? ሚሊዮኖች ተፈናቅለው፣ ንብረታቸው ተዘርፎና ወድሞ፣ ኑሯቸው ሲናጋ፣ እለት በእለት እያየንም እንኳ፣ ትንሽ ሰከን ብለን ማሰብ አንጀምርም? አሁንም ሰበብ አስባብ መደርደር?
መነሻው፣ ምንም ይሁን ምን፣ ጭፍን እምነትም ይሁን ሌጣ አላዋቂነት፣… ፖለቲካን እንደቁማር ጨዋታ የማየት ሞኝነትም ይሁን የአእምሮ ድንዛዜ፣ የዘረኝነት በሽታም ይሁን አልያም ሌላ መነሻም ይኑረው፣… የወንጀል ድርጊትንና ጥፋትን ለማቆንጀት፣ እንደ ልማዳዊ የእለት ስራ፣ ልማዳዊ ሰበቦችና ማመካኛዎች፣ በበቀቀን ደመነፍስ እየተነበነቡ፣ በሰላም መቀጠል አይቻልም – ወደባሰ ጥፋት ነው የሚያወርዱን።
“ይሄኛው ጥያቄ ተገቢ ነው። ያኛው አቤቱታ ትክክለኛ ነው። ተሰሚነት ማግኘት አለባቸው። መንግስት ተገቢ ጥያቄዎችን ካላደመጠ፣ ባለስልጣን ትክክለኛ አቤቱታዎችን ካልሰማ፣ ትልቅ ጥፋት ነው። በዚያ ላይ፣ ለአጥፊ ወንጀለኞች መንገድ ይከፍታል” ብሎ ማብራራት አንድ ጉዳይ ነው። እንዲሁ የምበደፈናው፣ “የህዝብ ጥያቄ” እያሉ ማነብነብ ግን፣ ጤናማ አስተሳሰብ አይደለም። በዚያ ላይ፣