እናቶችና ሴቶች መሬት ላይ እየተንከባለሉ አለቀሱ እየተጎተቱ ከአዳራሹ ወጡ፡፡
እስረኛው እና ቤተሠብ ተደበደበ፡፡
አባቶች ተገፈተሩ ተረገጡ ተመናጭቀው ከአዳራሹ ወጡ፡፡
ወጣቶች በዱላና በቡጢ ተደበደቡ፡፡
ተከሳሾች መሳሪያ ተቀባብሎባቸው ተቀጠቀጡ፡፡
በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱት ዛሬ በችሎቱ በተፈጠረ ችግር በርካታ አፈሙዝ ዞሮባቸዋል። በተከሳሾቹ ላይ ጥይት ሲቀባበልባቸው፣ አፈሙዝ ሲዞርባቸው ያዩ የተከሳሾች ቤተሰቦች ዋይታ አሰምተዋል። አልቅሰዋል።
አንዲት ዮናታን ተስፋዬ ሲያፅናናቸው የነበሩ እናት “እኔ ልቅደም፣ እኔን ቀድሞ ይግደለኝ” እያሉ ለተከሳሽ ልጃቸው ሲያለቅሱ ነበር። ብዙ እናቶች ሲያለቅሱ ነበር።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በጊኤያዊነት በ4ወንጀል ባስቻለው ችሎት 16 ተከሳሾች በማስረጃነት የቀረበባቸው ቃል በማሰቃየት የተገኘ ነው በማለት ቃላቸው በማስረጃነት እንዳይቀርብባቸው ውድቅ አድርጎታል።
በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ክስ መዝገብ የተከሰሱት 38 ተከሳሾች ብይን እየተነበበ ነው። ከቀረበባቸው 39 የአቃቤ ሕግ ምስክር መካከል እስካሁን የ6ቱ ተነብባል። የ7ኛ አቃቤ ሕግ ምስክር ቃል እየተበበ ነው።
በሌላ በኩል በቃጠሎው ሰበብ ተጠርጥረው ሸዋሮቢት ከተወሰዱ በኋላ ስቃይ የደረሰባቸው የ16 ተከሳሾች ቃል በማስረጃነት እንዳይቀርብባቸው ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል። ተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ምስክርነት እየተነበበ ነው።
ቃላቸው ውድቅ እንዲሆን የተደረገላቸው ተከሳሾች እና የደረሰባቸው ጉዳት
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱ 16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን ጉዳት በሪፖርቱ አኳትቷል። በዚህም መሰረት:_
ከበደ ጨመዳ:_ ቀኝ እጅ ላይ ትንሽ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር አውራ ጣት ስብራት፣
ኢብራሂም ካሚል:_ ቀኝ