Blog Archives

“ለኔ ብሄር ተኮር ልዩነቶች አይደሉም ትልቁ ጭንቀቴ …… ለኔ ትልቁ ጭንቀቴ ማህበረሰባዊ የግብረ ገብነት ወድቀት ነው።” ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ

“ትልቁ ጭንቀቴ ማህበረሰባዊ የግብረ ገብነት ወድቀት ነው” ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ነገ እሁድ ጷጉሜን 4 ወደ ሃገሪቸው የሚገቡ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ብሏል:- “ለኔ ብሄር ተኮር ልዩነቶች አይደሉም ትልቁ ጭንቀቴ። እውነቱ ለመናገር ብሄር ተኮር ልዩነት ፖለቲካዊ ጉዳይ ጉዳዩን ለማስተናገድ የሆነ መካኒዝም ልትፈልግለት ትችላለህ።  ይልቅ ለኔ ትልቁ ጭንቀቴ ማህበረሰባዊ የግብረ ገብነት ወድቀት ነው።” “You know the ethnic divisions are not my biggest worries to tell you the truth, because these are political issues that you can find mechanisms to accommodate. For me, the bigger worry is the moral collapse in the society. The degree to which people have literally lost their moral compass.…you know the absence of mechanisms of learning right from wrong. Making a distinction between what is right and what is wrong. Every society has to have some kind of a moral compass to exist. Our moral compass has been lost.” Berhanu Nega ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ ።  
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራን ትጥቅ የማስፈታት አዲሱ ስትራቴጂ! (ሙሉቀን ተስፋው )

አማራን ትጥቅ የማስፈታት አዲሱ ስትራቴጂ! (ሙሉቀን ተስፋው ) ባለፉት ዓመታት የወያኔ አገዛዝ የአማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ብዙ ጥሮ አልተሳካለትም ነበር፤ አሁን ያለው አደገኛ አካሔድ በጊዜ ካልተገታ ውጤቱ የከፋ ነው፡፡ ገበሬዎችን በገንዘብ በመደለል ትጥቃችሁን ፍቱ ማለት እጅግ ነውረኛ አካሔድ ነው፤ ሕወሓቶች መሣሪያ ከማስታጠቅም አልፈው ሁሉንም ትግሬ ወታደር ለማድረግ በሚነቀሳቀሱበት በዚህ ወቅት የአማራን ገበሬ በገንዘብ በመደለል ትጥቅ ለማስፈታት መሮጥ እጅግ እጅግ የከፋ መርዘኛ አካሔድ ነው፡፡ በበኩሌ ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት የአማራ ገበሬዎችን በየቦታው እየመዘገበ የእኔ ጦር የነበሩ ናቸው በማለት ሲያቀርብ አልተቃወምኩም ነበር፤ ምክንያቱ ደግሞ መንግሥት ለኦነግ ወታደሮች መቋቋሚያና ቤት ወዘተረፈ ለማቅረብ ስለተስማማ በዚህም የእኛ ገበሬዎች ተጠቃሚ ቢሆኑ ጉዳት የለውም ከሚል ነው፤ ይህም ብቻ ሳይሆን የአማራ ገበሬዎች አገዛዙ ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ የእነርሱንና የልጆቻቸውን ሕይወት ስለገበሩ መቋቋሚያ ማግኘት የግድ በመሆኑ በየትኛውም በኩል ይህን እገዛ ማግኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን አሁን አካሔዱ መስመር እየለቀቀ ነው፡፡ በዚህ ቀውጢ ጊዜ ነገሮችን ከመቼም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ሳይሆኑ የእኛን ገበሬዎች መቋቋሚያ ታገኛላችሁ በሚል መሣሪያና ትጥቅ ማስፈታት እጅግ አደገኛና ሁላችንም ልንቃወመው የሚገባ ነው፡፡ የግንቦት ሰባት አመራሮች ያሠማራችኃቸውን ወኪሎቻችሁን ይህን አደገኛ አካሔድ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ብታደረጉ መልካም ይመስለኛል፡፡ የአማራ ገበሬወችን ትጥቅ የማስፈታት ሒደት በእጅጉ እቃወማለሁ፡፡ ምስሉ የምዕራብ ጎጃም ገበሬዎች በግንቦት ሰባት የትጥቅ ማስፈታት ፕሮግራም ውስጥ እንዳሉ ነው የሚያሳየው፡፡
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተከሰው እስካሁን እስር ቤት የሚገኙት ተከሳሾች ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።

በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተከሰው እስካሁን እስር ቤት የሚገኙት ተከሳሾች ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ የመዝገብ ቁጥር 192368 ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት አዲስ አበባ ከሣሽ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ 2ኛ ተከሣሽ አቶ ግርማ ፍቃዱ ሞላ 33ኛ ተከሣሽ አቶ ሀብቶም ማማይ 3ኛ ተከሣሽ አቶ እሸቴ ዘለቀ መኮነን 38ኛ ተከሣሽ አቶ ገብረኪዳን መልካሙ አያሌው 4ኛ ተከሣሽ አቶ ለማ እሸቱ ዘገደ 42ኛ ተከሣሽ አቶ ሲሣይ መኮንን በቀለ 5ኛ ተከሣሽ አቶ አብርሃም ደርበው 43ኛ ተከሣሽ አቶ ወንድይፍራው አደራጀው ካሣይ 6ኛ ተከሣሽ አቶ መስፍን ሁሬሣ ተክሌ 49ኛ ተከሣሽ አቶ ላመነው ማሞ አለፈ 8ኛ ተከሣሽ አቶ ፀጋየ እሸቴ መኩሪያ 53ኛ ተከሣሽ አቶ ፍሬው ሞኝነት ካሣ 13ኛ ተከሣሽ አቶ ደሣለኝ ንጉሤ ሙላቱ 56ኛ ተከሣሽ አቶ ሰሎሞን አያሌው ዘነበ 14ኛ ተከሣሽ አቶ ሀብሉ አንገሶ ውንዴሣ 64ኛ ተከሣሽ አቶ እልፈቱ ፋሲካው ውብነህ 15ኛ ተከሣሽ አቶ በዛ ሙላው ውብነህ 68ኛ ተከሣሽ አቶ ሀብታሙ መለሰ ይርና 16ኛ ተከሣሽ ቴወድሮስ ይግዛው አራጌ 69ኛ ተከሣሽ አቶ ዓለሙ አለልኝ ብርሃኑ 18ኛ ተከሣሽ አቶ ገነቴ ተረፈ ዓለሜ 71ኛ ተከሣሽ አቶ ወርቁ ሞገስ ድረስ 20ኛ ተከሣሽ አቶ ደሴ ኃይሌ ጣሰው 73ኛ ተከሣሽ አቶ ነጋሽ መሐመድ ሀቢብ 25ኛ ተከሣሽ አቶ ግደይ ፀሐየ ይግዛው 75ኛ ተከሣሽ አቶ አሸናፊ አብርሃ ይርጋ 26ኛ ተከሣሽ አቶ ሰሎሞን እሸቴ ጌታሁን 76ኛ ተከሣሽ ረ/ሣ መኳንንት ዓለሙ መለሰ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዐቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱት ክስ ሊቋረጥ አይገባም ሲል ተከራከረ።

ዐቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱት ክስ ሊቋረጥ አይገባም ሲል ተከራክሯል (ጌታቸው ሺፈራው) የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአርበኞች ግንቦት 7 ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ ቢነሳም በስሙ የተከሰሰሱት ክሳቸው መነሳት የለበትም ሲል መከራከሩ ታውቋል። ዛሬ ሐምሌ 10/2010 ዓም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በአርበኞች ግንቦት 7 ከተከሰሱት እነ ሚፍታህ ሸሕ ሱሩር ክስ መዝገብ ከተከሰሱት 77 ግለሰቦች መካከል ያልተፈቱት 46 ተከሳሾች የቀረቡ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ክሳቸው መቋረጥ የለበትም ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱ የተወካዮች ምክር ቤት አርበኞች ግንቦት 7 ከፀረ ሽብር አዋጁ ስሙ እንዲነሳ ካደረገ በኋላ የሽብር ክሶች እንዲቋረጡ “የስራ መመርያ” ይተላለፋል ብሎ እየጠበቀ እንደነበር፣ ነገር ግን እንዳልደረሰው ገልፆአል። ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ድርጅት ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ መነሳቱን በመግለፅ መፈታት እንዳለባቸው ቢገልፁም ዐቃቤ ሕግ “ድርጊቱ የተፈፀመው የድርጅቱ ስም ከፀረ ሽብር አዋጁ ከመነሳቱ በፊት ነው። የድርጅቱ ስም ከአዋጁ በመነሳቱ ብቻ ክሳቸው ሊቋረጥ አይገባም። ክርክሩ መቀጠል አለበት።” ሲል ከፀረ ሽብር አዋጁ ስማቸው በተነሳለቀቸው ድርጅቶች ስም የተመሰረተው የሽብር ክስ መቋረጥ የለበትም ሲል ተከራክሯል። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፀረ ሽብር አዋጁ ክስ የተመሰረተባቸው ክሳቸው ተቋርጦ እንዲሁም በምህረት እንደሚፈቱ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። ከሶስት ቀን በፊት ከዐቃቤ ሕግ መስርያ ቤት የተወከለ ሰው ቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞችን ባወያየበት ወቅት በሽብር ተከስሰው ያልተፈቱት አቤቱታ ሲያቀርቡ “በዚህ ክስ ተከስሶ እስካሁን እስር ቤት ያለ ሰው ስለመኖሩ አናውቅም” የሚል መልስ እንደሰጣቸው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አርበኞች ግንቦት ሰባት ለውጥ ለማምጣት ተገዶ የገባበትን ማንኛውንም ሰላማዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ ማቆሙን አወጀ ።

በሃገራችን የዲሞክራሲ ለውጥ ለማምጣት ተገደን የገባንበትን ማንኛውንም ሰላማዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ ገተናል። የአርበኞች ግንቦት 7 ልዩ መግለጫ:- ” የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት በርካታ አመታት ከአፈና አገዛዝ ለመላቀቅና ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ለመሸጋገር እልህ አስጨራሽ ትግል በማካሄድ ላይ ይገኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝባችን ትግል የወለደውና በኢህአዴግ ውስጥ ታፍኖ ይኖር የነበረው የለውጥ ሃይል ይህንን ትግል ተቀላቅሎ በዋነኛነት ትግሉን የመምራት ሃላፊነት እየተወጣ ነው። ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ከትናንት በስቲያ ሰኔ 13 ቀን 2010 ዓም ባወጣው መግለጫ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ህዝብና ይህን ለውጥ ከሚመራው ወገን ጎን እንደሚቆም በማያሻማ ቃላት ግልጽ አድርጓል። መግለጫችን ደጋግሞ ለማስረዳት እንደሞከረው አርበኞች ግንቦት 7 ከማናቸውም አመጾች ነፃ የሆነ ሰላማዊና የሰለጠነ የፖለቲካ ትግል ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ ሊወስደን የሚችል አስተማማኝ የትግል ስልት መሆኑን አስገንዝቧል። በሃገራችን የአመጽ ትግል አስፈላጊነት የመነጨው ራስን ከአሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ለመከላከል ሲባል ብቻ የተወሰደ አማራጭ ያልነበረው መፍትሄ በመሆኑ ነበር ። ኢህአደግ ውስጥ የተነሳውና በጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ የሚመራው የለውጥ ሃይል እየወሰደ ባለው እጅግ አበረታች እንቅስቃሴ የሃገራችንን ፖለቲካ ከአመጽ ነጻ በሆነ ሰላማዊ እና ስልጡን ፖለቲካ ከግብ ማድረስ እንደሚቻል ተስፋ ስለፈነጠቀ፤ እየታየ ያለውን አበረታች እንቅስቃሴ ለማገዝ ሰኔ 8 እና 9 ልዩ ስብሰባውን ያካሄደው የንቅናቄያችን ሥራ አስፈጻሚ ወቅታዊውን ሁኔታ ከገመገመ ቦኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፎአል። ከዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አርበኞች ግንቦት 7 በማናቸውም መልኩ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ምንም አይነት አመጽ ነክ እንቅስቃሴ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለኢቲቪ ቃለ ምልልስ ሰጡ ።(ቪድዮ)

$bp("Brid_24422_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/Facebook-1972985102733356.mp4", name: "የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለኢቲቪ ቃለ ምልልስ ሰጡ ።(ቪድዮ)", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/06/IMG_20180621_160027.jpg"}, "width":"550","height":"309"}); EBC የአርበኞች ግንቦት 7 ባወጣው መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቀረበው የሰላም ሃሳብ እንደሚቀበልና ለተግባራዊነቱም የበኩሉን እንደሚያደርግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ዶ/ር ዐቢይና የለውጥ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በቆም በሚያደርጉት ትግል አብሯቸው መሆኑንም ገልጿል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ የሰጡትን የዲሞክራሲ ተስፋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችል የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ገለጸ።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የትጥቅ ትግሌን ላቆም እችላለሁ አለ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ የሰጡትን የዲሞክራሲ ተስፋ ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ የትጥቅ ትግሉን ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ። ንቅናቄው የሰለጠነ ፖለቲካ የምንመርጠው ፣ የምናውቀውና የምመኘው የትግል ስልት ነው በሚል ባወጣው መግለጫ እንዳለው አርበኞች ግንቦት ሰባት የመሳሪያ ትግልን ዋነኛ የትግል ስትራቴጂው በማድረግ የፖለቲካ ስልጣን የመያዝ አላማ ኖሮት አያውቅም። ሆኖም ግን አገዛዙ ይከተለው በነበረው ኋላ ቀር ፖለቲካ ምክንያት ዜጎች ከመንግስት ሽብር ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሲያበረታታና እራሱንም ከጥቃት ሲከላከል ቆይቷል ብሏል በመግለጫው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሰሞኑን ለፓርላማ ያደረጉት ገለጻ የሚያበረታታና የሚደነቅ ሲል አወድሶታል። መንግስት የሽብር ተግባር ይፈጽም እንደነበር ዶክተር አብይ በይፋ መናገራቸውና የፍትህ ስርአቱ ችግር ያለበት መሆኑን ማመናቸው ሃቅን ለመናገር የሚደፍሩ መሪ መሆናቸውን ይሳያል ሲል ንቅናቄው ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ይህ ብቻ አይደለም እሳቸው የሚመሩት ቡድንም ለሃገራዊ መግባባት ያለውን ዝግጁነትም ያሳያል ብሏል አርበኞች ግንቦት ሰባት። ዶክተር አብይ በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን ክልል የሚያጠና ኮሚሽን ይቋቋማል ማለታቸውንም አዎንታዊ ነው ሲል በመግለጫው አመልክቷል። ሕወሃትንና የትግራይን ሕዝብ ለይቶ ስለመመልከት ዶክተር አብይ አህመድ የተናገሩትም አርበኞች ግንቦት ሰባት ከልብ የሚያምንበትና በጽናት ሲያራምደው የቆየ እምነት መሆኑንም ገልጿል። እንደ አርበኞች ግንቦት ሰባት መግለጫ ከሆነ በሕወሃት ውስጥ የለውጥ ሃይሎች መኖራቸው እሙን ነው። እናም የኢትዮጵያን ሰቆቃ በመቀነስ ረገድ ሕወሃት ውስጥ ያሉ የለውጥ አራማጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን እናምናለን ብሏል አርበኞች ግንቦት
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰለጠነ ፖለቲካ የምንመርጠው ፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው ። የአርበኞች ግንቦት 7 ልዩ መግለጫ

የሰለጠነ ፖለቲካ የምንመርጠው ፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው ። የአርበኞች ግንቦት 7 ልዩ መግለጫ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News