Blog Archives

የኤሌክትሪክ ታሪፍ በአራት እጥፍ ለመጨመር ማሰብ በበደል ላይ በደል ደሃውን መግደል ነው ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው።

 ምንሊክ ሳልሳዊ – የኤሌክትሪክ ታሪፍ በአራት እጥፍ ለመጨመር ማሰብ በበደል ላይ በደል ደሃውን መግደል ነው። ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው። ከካርታው የፖለቲካ ቁማር ይልቅ በደሀው ሕዝብ ላይ የሚጨመር የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ አሳሳቢ ነው። ለራሳችን ሳናውቅ ለጎረቤቶቻችን የምንሸተው የኤሌክትሪክ ፍጆታ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል። ይህ ችግር ፋብሪካዎችና ተቋማት ስራ ከማቆም ጀምሮ ሰራተኞችን አስከመበተን ዘልቋል። የተበተነው ሰራተኛ ቤቱም ሔዶ ኤሌክትሪክ የለውም ፤ በወር የኤሌክትሪክ ፍጆታውን እንደተጠቀመ ሰው ግን የደሃ ገንዘቡን በመንግስት ይነጠቃል። ይህ አደገኛ አካሔድ መንግስትን ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም። የኤሌክትሪክ ፍጆታን በአራት እጥፍ መጨመር ማለት አብዛኛው ደሃ በሆነባት ሃገር ውስጥ በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል ይሆናል። ኢትዮጵያ ከጎረቤትም ሆነ ከሌሎች ሀገራት ለኤሌክትሪክ ኃይል የምታስከፍለው ታሪፍ አነስተኛ ስለሆነ ይህንን ደሃ ሕዝብ መብራት በማሳጣት ብቻ ሳይሆን ታሪፍም በመጨመር ማማረር ያስፈልጋል የሚል አቋም የያዘው መንግስት ለጎረቤት ሃገራት በርካሽ እየሸጡ ለዜጎች ሲሆን ሀገሪቱ አሁን እያስከፈለችው ባለው ታሪፍ ጥራቱን የጠበቀ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ የማይቻል ነው በማለት አቅርበው የማያውቁትን ጥራት ሰበብ በማድረግ በፖለቲካና በኢኮኖሚ የደቀቀውን ሕዝብ ሊያሰልሉት እያሟሟቁ ነው። ዜጎችን በጨለማ እያሳደሩ ለጎረቤት አገሮች ኤሌክትሪክ በመሸጥ ገንዘቡን በሙስና የሚቀራመቱ መሆኑን በተደጋጋቢ ተሰምቷል ፤ ካሁን ቀደም የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመብራት ሃይል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ አስናቀ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ጀርመን አገር በሚገኝ ባንክ ማስቀመጣቸው የሲአይኤ ሰነድ ዋቢ አድርገው አምባሳደር ያማማቶ ለዶክተር አብይ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ሊነሱ ነው

ዋዜማ ራዲዮ– የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ከሀላፊነታቸው ሊነሱ ነው።የኢንጂነር አዜብ መነሳት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የልማት ተቋማትን የማሻሻል አንዱ አቅጣጫ መሆኑ ተጠቅሷል። በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ በኩል ውሳኔው መተላለፉን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ነግረውናል። ሌሎች የመንግስት ድርጅቶች ሐላፊዎችንም ለመተካት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ስምተናል።ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ወደ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፈጻሚነት ከመምጣታቸው በፊት የግልገል ጊቤ ሶስት የውሀ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ነበሩ። 10 አመት የወሰደውና 1.5 ቢለዮን ዪሮ ወጭ ሲገነባ የነበረው የግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ ብዙ የግንባታ ሂደት ሳይጠናቀቅ ነበር የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ሀይልና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተብሎ ለሁለት ሲከፈል የሀይሉን ዘርፍ በዋና ስራ አስፈጻሚነት የያዙት። ኢንጂነር አዜብ ወደዚህ ሀላፊነት ከመጡ ወዲህ ራሳቸው በስራ አስኪያጅነት ሲመሩት ከነበረው ጊልገል ጊቤ ቁጥር ሶስትና ከአዳማ ቁጥር 2 የንፋስ ሀይል ማመንጫ ውጭ ወደ ስራ የገባ ፕሮጀክት የለም።ኢንጂነር አዜብ በ2006አ ም ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ስራ አስፈጻሚነት የመጡት በወቅቱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በነበሩት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ግፊት እንደሆነ ይነገራል። እሳቸው ወደዚህ ሀላፊነት ከመጡም በሁዋላ በሀይል አቅርቦት ይህ ነው የተባለ ለውጥ በሀገሪቱ አልመጣም። ይልቁንም በኢትዮጵያ በሀይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ትልልቅ ተቋማት ለመስራት የተቸገሩበት እና ተገንብተውም ወደ ስራ መግባት ያልቻሉበት ሁኔታ ጎልቶ ታይቷል። በሌላ በኩል በኢንጂነር አዜብ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News