የኤሌክትሪክ ታሪፍ በአራት እጥፍ ለመጨመር ማሰብ በበደል ላይ በደል ደሃውን መግደል ነው ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው።

 ምንሊክ ሳልሳዊ – የኤሌክትሪክ ታሪፍ በአራት እጥፍ ለመጨመር ማሰብ በበደል ላይ በደል ደሃውን መግደል ነው። ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው።

ከካርታው የፖለቲካ ቁማር ይልቅ በደሀው ሕዝብ ላይ የሚጨመር የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ አሳሳቢ ነው። ለራሳችን ሳናውቅ ለጎረቤቶቻችን የምንሸተው የኤሌክትሪክ ፍጆታ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል። ይህ ችግር ፋብሪካዎችና ተቋማት ስራ ከማቆም ጀምሮ ሰራተኞችን አስከመበተን ዘልቋል። የተበተነው ሰራተኛ ቤቱም ሔዶ ኤሌክትሪክ የለውም ፤ በወር የኤሌክትሪክ ፍጆታውን እንደተጠቀመ ሰው ግን የደሃ ገንዘቡን በመንግስት ይነጠቃል። ይህ አደገኛ አካሔድ መንግስትን ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም።

የኤሌክትሪክ ፍጆታን በአራት እጥፍ መጨመር ማለት አብዛኛው ደሃ በሆነባት ሃገር ውስጥ በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል ይሆናል። ኢትዮጵያ ከጎረቤትም ሆነ ከሌሎች ሀገራት ለኤሌክትሪክ ኃይል የምታስከፍለው ታሪፍ አነስተኛ ስለሆነ ይህንን ደሃ ሕዝብ መብራት በማሳጣት ብቻ ሳይሆን ታሪፍም በመጨመር ማማረር ያስፈልጋል የሚል አቋም የያዘው መንግስት ለጎረቤት ሃገራት በርካሽ እየሸጡ ለዜጎች ሲሆን ሀገሪቱ አሁን እያስከፈለችው ባለው ታሪፍ ጥራቱን የጠበቀ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ የማይቻል ነው በማለት አቅርበው የማያውቁትን ጥራት ሰበብ በማድረግ በፖለቲካና በኢኮኖሚ የደቀቀውን ሕዝብ ሊያሰልሉት እያሟሟቁ ነው።

ዜጎችን በጨለማ እያሳደሩ ለጎረቤት አገሮች ኤሌክትሪክ በመሸጥ ገንዘቡን በሙስና የሚቀራመቱ መሆኑን በተደጋጋቢ ተሰምቷል ፤ ካሁን ቀደም የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመብራት ሃይል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ አስናቀ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ጀርመን አገር በሚገኝ ባንክ ማስቀመጣቸው የሲአይኤ ሰነድ ዋቢ አድርገው አምባሳደር ያማማቶ ለዶክተር አብይ ካቢኔ ሰዎች መናገራቸውን ሰምተናል። አንድ የ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ሊገነባ የሚችል ገንዘብ የሚዘርፉ የመብራት ኃይል ባለስልጣናት በደሃው ላይ ሴራ መጎንጎን ሊያቆሙ ይገባል። ሕዝቡ ታሪፉን ተከትሎ ለሚያነሳው ሕዝባዊ አመፅ ተጠያቂው መብራት ኃይል ነው። መንግስት የሚስነው ውሳኔ የዜጎችን መብትና አቅም ማገናዘብ አለበት።

በበደል ላይ በደል የከሳውን መግደል ይቁም !!!  ምንሊክ ሳልሳዊ