Blog Archives

እየታየ ያለው ለውጥ፤ የቅርጽ ወይስ የይዘት? – ብርሃኑ አበጋዝ

ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ – አዲስ አበባ ጭብጥ *** የጽሑፌ ጭብጥ፣ አሁን በአገራችን እየታየ ያለው ለውጥ የቅርጽ እንጂ የይዘት አይደለም የሚል ነው፡፡ መግቢያ *** አንድ፣ ተርታው (ordinary) ዜጋ ሳይቀር እተገነዘበው የመጣ ሐቅ አለ፡፡ ይህም ሐቅ ገዥውን ግንባር የተመለከተ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ደንብሿል፤ አርጧል፤ አዲስ ሐሳብ ማመንጨት አይችልም፡፡ ይኽ እውነት ነው፡፡ ገዥው ግንባር ዘመኑን የዋጀ ሐሳብ የሚያፈልቅ አዲስ ኀይል ማፍራት የማይችል ድርጅት ሆኗል፡፡ አሁንም የድርጅቱ ከፍተኛም ይኹን ዝቅተኛ አመራሮች አቶ መለስ ባዘጋጇቸው መጻሕፍት ነው ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት፡፡ አዲስ ራዕይ የተባለው የድርጅቱ የንድፈ-ሐሳብ መጽሔት ሳይቀር አቶ መለስ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ያዘጋጇቸውን ጽሑፎች እንደገና እየቀባባ ማወጣት ጀምሯል፡፡ ጥልቅ ተሐድሶ የሚለው “አዲሱ” የኢሕአዴግ መርሐ ግብርም በአቶ መለስ አስተምህሮዎች ላይ የተንጠለጠለ እና የእሳቸውን ጽሑፎች መሠረት ያደረገ ነው፡፡ የሚገርመው የገዥው ግንባር መሪዎች ለስልጠና ሳይቀር አቶ መለስ የተናገሯቸውን ንግግሮች (ቪዲዮዎች) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡ አሁንም የሐሳቡ አምንጭም አሰልጣኙም አቶ መለስ ናቸው፡፡ አንዳንዴም በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሳይቀር የአቶ መለስ ንግግሮች ይቀርባሉ፡፡ ጥልቅ ተሐድሶ በሚባለው መርሐ ግብር ከቀረቡት ነጥቦች ውስጥ “መስመር መሳት” የሚል ይገኝበታል፡፡ መስመር መሳት የተባለውም በአቶ መለስ የተዘጋጁትን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች መተው ማለት ነው፡፡ አዲስ ሐሳብ፣ ከዘመኑ ጋር ሊሄድ የሚችል አቀራረብ ከድርጅቱ መስመር እንደመውጣት ይቆጠራል፤ ያስገመግማል፡፡ “ዴሞክራሲያዊ ልማታዊነት እና/ወይም አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ከሚባለው መስመር ውጭ የሚታሰብ ነገር የለም፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮችም ሆኑ አፈ ጮሌ (እና አድርባይ) ካድሬዎች የሚናገሩት ሁሉ የዛገና አዲስ ነገር
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News